👉 ለአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የሚደርስ ጥብቅ መልዕክት! 🏗️⚠️

​አዲስ አበባ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት በተቀመጡ መሬቶች ላይ የመጨረሻ ዕርምጃ ልትወስድ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ከተማዋ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት እንዳልሆነች አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

​ቁልፍ ጉዳዮች እና የተወሰኑ ውሳኔዎች፡
​በታጠሩ መሬቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ፦

አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ቀደም ሲል የተደረሰውን መግባባት ጥሰው መሬት አጥረው በሚያስቀምጡ አካላት ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፤ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ዕድልም አይሰጥም።

​የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም፦

የከተማዋን ገቢ አሰባሰብ ለማዘመን በተከናወነው ሥራ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአፍሪካ መልካም አሠራር አላቸው ከተባሉ 6 ከተሞች መካከል አንደኛ መውጣቱ ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥናት ተረጋግጧል።

​የመሠረተ ልማት እና ጤና ዘርፍ እምርታ፦

ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የጤናና የመሠረተ ልማት ሥራዎች (በአልጋ ቁጥር፣ በሕክምና መሣሪያዎችና ተቋማት ይዘት) ከዚህ ቀደም ከተሠሩት ጋር ሲነፃፀሩ በእጥፍ ማደጋቸው ተገልጿል። እንዲሁም የከተማዋን ሰላም ለማስከበር የተሠሩ ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ አስችለዋል።

ይህ የመሬት አጠቃቀም ቁጥጥር እና የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ አቋም በኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚኖረው በመሆኑ፣ ባለሀብቶችና የዘርፉ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

​🚧ለተጨማሪ መረጃና የዘርፉ ትንታኔዎች ሌላኛው የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ👇

https://t.me/ETCONpWORK

Comments

Be the first to add a comment