👉በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እየተከፈቱ ነው።

🚧ከ1,140 በላይ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተከፍተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከታህሳስ 14 ጀምሮ በ1 ሺህ 143 ሥፍራዎች የተዘጉ መንገዶችን በማስከፈት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል፡፡

400 የሚሆኑት በግብረ-ኃይል እንዲነሱ የተደረገ ሲሆን፣ 720 የሚሆኑት ደግሞ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ህብረተሰቡ በራሱ ያነሳቸው ናቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 685 ኮለኖች እና 11 ኬላዎችም በግብረ ኃይል የዘመቻ ሥራ ተነስተዋል፡፡

በቀጣይም ህብረተሰቡ በራሱ ጊዜ አጥሮችን እንዲያነሳ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በድጋሚ አሳስቧል፡፡

Via አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp

Comments

Be the first to add a comment