👉ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአዲስ አበባ 5 ዘመናዊ  ሆቴሎችን ሊገነባ ነው።

💫ሆቴሎቹ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🚧ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ኤ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነና የሸራተን አዲስ ሆቴልን ስያሜ የሚይዝ ሌላ ሆቴል ይገነባል።

🚧በሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ዘመናዊ ሆቴል (Moxy by Marriott) ፣ በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴሎች ይገነባሉ።

🚧በቅርቡ የሚድሮክን ቤተሰብ የተላቀለው ዋቢሸበሌ ሆቴል (autograph collection by Marriot) ደረጃ ለጉባኤው ዝግጁ ይሆናል።

🚧አፍሪካ ህብረት አጠገብ እየተገነባ ያለው ዌስት ኢን አዲስ (Westin Addis) ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

🏷ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለ32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች 1500 አልጋ ያላቸው ሆቴሎችን እንደሚገነባ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።

⏺በተጨማሪም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በክልል ከተሞች በጂማ እና ሃዋሳ (Four Points by Sheraton) ሆቴሎችን እየገነባ ይገኛል።

⏺በባህርዳር ከተማ ደግሞ (Four Points by Sheraton) እና (Protea by Marriott) ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል።

⏺ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ የላንጋኖ ሳቫና ሪዞርትን በግዥ የተረከበው ሲሆን በማርዮት ብራንዶች አለም አቀፍ ሪዞርት በመገንባት ወደ ስራ ይገባል።

⏺ባሳለፍነው ሳምንት የኤኮ ቱሪዝም ዘርፉን ከፍ ሊያደርግ የሚችለውን የደንቢ ኤኮ ሎጅ በማስመረቅ ወደ ስራ አስገብቷል ።

Via Midroc Investment Group

@etconp

Comments

Be the first to add a comment