የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ከኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆችና አላማዎች ውስጥ የኢኮኖሚ ነክ አላማዎች፥
አንቀፅ 89
ኢኮኖሚ ነክ አላማዎች
መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት ፡፡
መንግስት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና በሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት ፡፡
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፡፡
በእድገት ወደኋላ ለቀሩ ብሔሮች፣ብሔረ ሰቦች፣ሕዝቦች መንግስት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
መንግስት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ፡፡
የሀገር ልማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግስት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት፡፡ የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት፡፡
መንግስት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ለልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡
መንግስት የሰራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት፡፡
አቃቤ ሕግ አሊ ሳፊ
ጥቅምት 04/2015ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment