🏠ለመኖሪያ ቤት የሚሰራ ደረጃ ቢያንስ ስንት ስፋት ሊኖረው ይገባል?

🔆ቤት ሲነደፍ ብዙ ጊዜ ትኩረት የሚሰጠው በክፍሎች መጠን ላይ ብቻ ነው። ነገር ግን የደረጃ ስፋት (Staircase Clear Width) ለደህንነት፣ ለምቾት እና ለቀላል የሰው እንቅስቃሴ በጣም ወሳኝ ነው።

📌 በተጠቀሰው ስታንዳርድ መሠረት፦

🔹 ለግል መኖሪያ ቤት (Private Residential Building)
የደረጃው አነስተኛ የጽዳት ስፋት 90 cm (0.90 m) መሆን አለበት።

🔹 ለጋራ መኖሪያ እና ለሕዝብ/ንግድ ህንፃዎች
በአጠቃላይ 1.20 m እስከ 1.50 m የሚደርስ ስፋት ይፈለጋል። ይህም በተለይ የሰው እንቅስቃሴ ሲበዛ እና በአደጋ ጊዜ ህንፃውን በፍጥነት ለመልቀቅ ጠቃሚ ነው።

⚠️ በሳይት ላይ ይህን ነገር አትርሱ!

1️⃣ Plaster & Tile Allowance
የደረጃውን ስፋት ሲያስሉ የፕላስተር፣ የማርብል ወይም የግራናይት አጨራረስ የሚወስደውን ቦታ ግምት ውስጥ ያስገቡ። የሚፈለገው Clear Width ከአጨራረስ በኋላ የሚቀረው ስፋት መሆኑን አይዘንጉ።

2️⃣ Headroom Height
ከደረጃው መረገጫ እስከ በላይኛው ኮንክሪት/ጣሪያ ያለው Headroom ቢያንስ 2.10 m መሆኑን ያረጋግጡ።

👷 ትንሽ የሚመስል የደረጃ መጠን ስህተት በኋላ ለማስተካከል ትልቅ ወጪ ሊያስከትል ይችላል ስለዚህ ከግንባታ በፊት በዲዛይን ደረጃ በትክክል ማስላት አስፈላጊ ነው።

🌟እርስዎ የሚገነቡት ቤት የደረጃ ስፋት ስንት cm ነው? ከታች ያሳውቁን!

👉ደረጃ (Stair Case) ስትራክቸራል ዲዛይኑ በቀላሉ ለመስራት ከታች ባለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a664a8fafe65_etconp

Comments

Be the first to add a comment