👉የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስባቸው አራት áˆáŠ­áŠ•á‹Ťá‰śá‰˝:-

💫በፌደራል ግዥ አዋጅ 1333/2016 መሠረት በማንኛውም ተጫራች የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊወረስ ይችላል።

1)ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ጨረታው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ካገለለ ወይም፣

2) ጨረታው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ ተጫራች መሆኑ በፅሑፍ ተገልጾለት፣ ውል ለመፈረም፣ የገዛውን ንብረት ለማንሳት ወይም የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ 

3) በተጫራቹ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ላይ የሂሳብ እርማት ተደርጎ ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፤

4) ተጫራቹ የማጭበርበር ወይም የማታለል ወይም ከሌሎች ተጫራቾች ጋር የመመሳጠር ወይም መረጃ የመደበቅ ድርጊቶችን መፈፀሙ ሥልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ ከሆነ ናቸው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment