👉ኢትዮጵያ የምትጠቅምባቸው የኮንስትራክሽን ሕጎች!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማስተዳደር የምትጠቀምባቸው አዋጆች (Decree)፣ ደንቦች (regulations)፣ መመሪያዎች (Directives)፣ ስታንዳርዶች (Manuals)፣ የውል ሰነዶች (Contract Conditions)፣ ህጎች (Laws and codes)፣ ጋዜጦች (Negarit) አሏት። እነዚህን ማሕቀፎች በሁለት ምድብ መመደብ (ዓለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ) ማለት እንችላለን።
1. በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የኮንስትራክሽን ውል ማህቀፎች፦ FIDIC MDBS (Federation Internationale Des Ingenieurs-Conseils)፣ EU condition of contract፣ NEC- new engineering contract, UK (በተለይ ለውኃ ቁፋሮ ውል የሚውል) ናቸው። ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ማኑዋሎችን እንደ መሪ ልኬት (በተለይ የግንባታ ግብአቶችን ጥራት በቤተሙከራ ለመለካት) እንጠቀማለን።
ከእነዚህም ውስጥ:- American Society Testing Materials (ASTM), American Association of State Highway and Transportation Officials (AASHTO) ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ Indian Standards (IS) እና British Standard (BS) አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው።
2. የሀገር ውስጥ ማሕቀፎች፦ Building and Transport Construction Design Authority (BaTCoDA - የግንባታ ሥራዎችንና ግብአቶችን መጠን ለማስላት)፣ Public Procurement Agency (PPA - ለጨራታ እና የስምምነት ውል ሰነድ አስተዳደር)፣ Civil Code, Civil Procedural codes, Ministry of Works and Urban Development Standard Conditions of Contract (MOWUD Directives), FDRE constitution, ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ (Negarit Gazieta), በየጊዜው የሚሻሻሉ የሕንጻ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች፣ የሙያ እና የሥራ ፍቃድ አዋጆች የመሳሰሉት ይገኙበታል።
በእርግጥ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ አይችሉም የሚባሉ የሀገሪቱ ህጎች አይኖሩም ማለት ይከብዳል፣ ምክንያቱም ሁሉም ህጎች ከቦታ፣ ከሥራ፣ ከሰው ኃይል፣ ከመብትና ግዴታ፣ ከንብረት፣ ከወንጀልና ፍትሕ ጋር የተያያዙ ስለሆነ እና የኮንስትራክሽ ሴክተሩም እነዚህ ሁሉ የሚገኙበት ኢንዱስትሪ ስለሆነ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━
👉የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ እና አተገባበሩ | የተግባር መመሪያ መፅሐፍ ይፈልጋሉ?
📚 ይህ መፅሐፍ በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮችን በቀላልና ተግባራዊ መልኩ ለመረዳት ይረዳል።
⏺የኮንስትራክሽን ሕግ መሠረታዊ ግንዛቤ
⏺የግንባታ ፕሮጀክት ሕጋዊ አተገባበር
⏺የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታ
⏺የኮንትራት እና የስምምነት ጉዳዮች
⏺የግንባታ ሥራ ኃላፊነትና ተጠያቂነት
⏺በግንባታ ሥራ ላይ የሚፈጠሩ የሕግ ጉዳዮች እና ሌሎች ተካተዋል
👇
https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a83e1c10064f_etconp