የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
አዲሱ የፅዳት ህግ
‼️
ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት የሚጥለው ረቂቅ አዋጅ ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ተገለፀ
‼️
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል።
ረቂቅ አዋጁ ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት እንደሚጥልና አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች እንደሚከላከል ተገልጿል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ ረቂቅ አዋጁ አገር የጀመረችውን ፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለአሰባሰብ አዳጋች እና አካባቢን በመበከል ማህበረሰቡን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየዳረጉ ስለሆነ መቆም አለባቸው ብለዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ፈቲያ አሕመድ ረቂቅ አዋጁ ረዥም ዘመናት ማገልገል እንዲችል በርካታ ባለድርሻዎችን ያካተተ ውይይት በቀጣይነት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።
ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጁ መዘጋጀቱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
#Ethiofm
Comments
Be the first to add a comment