የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
152.pdf
1.1 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ስራዎች ድርጅት ለማቋቋም የወጣው ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡
።።።።።።።።።
የንግድ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና የነዋሪው ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ሌሎች በአለም አቀፍ እና በሀገሪቱ ውስጥ በተፈጠሩ የተለያዩ ምክንያቶችን ተከትሎ የግብርና እና የኢንዲስቱሪ ምርቶች ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ለኑሮ ውድነት የተጋለጠ ሲሆን መንግስት በከተማው የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የንግድ ስራዎችን ለማቋቋም ደንብ አውጥቷል፡፡
የከተማው አስተዳደር ለከተማ ነዋሪው በተፈጠረው የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች የግብርና እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የንግድ ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በቀጥታ ከአርሶ አደሩ በመግዛት የሚያቀርብ ደንብ ቁጥር 152 /2015 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ከህግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ለማወቅ ተችሏል፡፡
Comments
Be the first to add a comment