بسم الله الرحمن الرحيم

               سلامٌ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الهُدَى

"በዚህ፦ በቪዲዮ scroll ዘመን? ፅሁፍ!?" ይባላል መቼስ¡
አብሽሩ እንደምንም ይነበብ!

ሰዎች
◇ ከፈጣሪያቸው አላህ ጋር እንዲተዋወቁና እሱን ችላ እንዳይሉት፣
◇ የተፈጠሩበትን አላማ ረስተው በሌላ ውዳቂ በሆነ ነገር እንዳይጠመዱ፣
◇ መልካም ስራዎችን በሚችሉት እንዲሰሩ፣ ከመጥፎ ነገርና ከወንጀል እንዲርቁ፣
የሚያስታውሱና የነብያቸውን ሙሐመድ ﷺ ስራ የሚያስቀጥሉ፦
በየቦታው፣ በየጊዜው፣ በተለያየ ቋንቋ ለኢስላም ዲን የሚለፉ የምድር ከዋክብት የሚባሉ ሰዎች አሉ ولله الحمد
(በማውራት ብቻም አይደለም ባላቸው ተሰጥኦና አቅም)። 

እንደ ከዋክብት
✨ ጌጦች፣ ለምድር ውበት ሰጪዎች ናቸው፤ አላህ ወደ ታች ሲያይ ምድር እንድታምረው ያደርጋሉ፤
✨ ሰዎች መሄጃ ጠፍቷቸውና ግራ ተጋብተው መንገድ እንዳይስቱ አቅጣጫ ይጠቁማሉ፤
✨ አጥፊዎችና ሰውን የሚያጠሙ የሰው ሸይጣኖች ላይ ሚሳኤል የሆኑ ንግግሮችን እያስወነጨፉ ከምድረ ገፅ ቆሻሻዎችን ያፀዳሉ።

ይሄ አላህ ዘንድ ከምንም በላይ ተፈላጊና ተወዳጅ ነገር ነው።
ራሳቸው ላይ ስራ የሚሰሩ ከመሆናቸውም ጋር ከራስ አልፎ የሌሎች ሰዎች ህይወት እንዲያምር ልባቸውና አስተሳሰባቸው ንፁህ፣ ባህሪያቸውና የሚሰሩት ስራ መልካም እንዲሆን የሚታገሉ ሰዎች አላህ ዘንድ ሲቀጥልም ሰዎች ጋር ትልቅ ቦታ አላቸው።

በእርግጥ ይሄ ዝም ብሎ አፍና ጣት ስላለ ብቻ የሚገባበት ነገር አይደለም።
የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ፦
◇ ኢኽላስና በነብያት መንገድ፣
◇ እውቀት፣
◇ መልካም ስነምግባር፣
◇ የመልዕክቶችን ግርማ ሞገስና ውበት አስጠብቆ ማስተላለፍ፣
◇ ነገራቶችን ማመዛዘን፣
◇ ከስሜታዊነት መራቅ፣
◇ ለሰዎች አሳቢና አዛኝ መሆን

እኚህና ሌሎችም መሰል ነገሮች መኖር አለባቸው።
ይሄን ጠብቀው የሚታገሉ ሚታወቁም ማይታወቁም ውድ የአላህ ባሪያዎች አሉ።

ግን አሁን ላይ ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ተናጋሪ ሆኗል፤ ቤቱንና ሱቁን ስቱዲዮ አርጎታል።
ቲክቶክና ዩቲዩብ ስለሚከፍሉ በሚል ያገኙትን አውርተውና ሰርተው ቪዲዮ ሚለቁ አንዳንዴ የሚያሳፍርና የማይጠበቅ ነገር ሚያደርጉ "ብቻ የለቀቅኳት ነገር (view) እይታ ታግኝ፣ ብር ታምጣ" እያሉ ዝነኛና ተከፋይ ለመሆን በሚል እሳቤ በጣም ከባድና የሚደብር፣ ከጉርምስናና ከወጣትነት እድሜ ሲታለፍ የሚያሳፍር "ምን ነክቶኝ ነው ይሄን ያደረኩት" የሚያስብልና የሚየስቆጭ ስራ የሚሰሩ፣ እኛው አጥር ግቢም (ኢስላምም ስር) ያሉ ይሄን የሚያደርጉ ሰዎች አሉ።
       አላህን እንፍራ!!


መልካም ነገር ማሰራጨት እየተቻለ፣ በራስ ሌሎችን የመጥቀም አቅሙ እንኳን ባይኖር ሌሎች የሰሩትን መልካም ነገር ማስተጋበት ምን ከለከለ!? ዝነኝነት በመጥፎ ነገር አይፈለግም፤ ሰዎች ዘንድ እንደምንም እንዴትም ታውቆ አላህ ዘንድ በመጥፎ የሚታወቅ ሰው ለምን ይኮናል?
ካስተዋልነው አብዛኛው ሰው በዚህ ቢዚ ሆኗል።
ኡማውን አላህ ያስተካክልልን፤ ልቦና ይስጥልን፤

ችላ መባል የሌለበትም ነገር!፦ ተመልካችና scroll አድራጊ ብቻስ ከመሆን፦ ጠንከርና ጠንቀቅ ተብሎ፣ አቅሙን እንዲሰጥ አላህን ለምኖ በኢኽላስ የሆነች መልካም ነገር አበርካች ለምን አይኮንም? ስለኢስላም ዳዕዋ ማድረግ ብቻም አይደለም (እንደ ግብ እሱ ሆኖ) ግን አላህ የሰጠንን "የሆነ" እኛ አልታይ ያለንን፣ ብርድ ልብስ ሸፍነን ይቀመጥ ያልነውን አቅም ተጠቅመን ራስን፣ ሙስሊሞችንና ሌሎችንም ሰዎችን መጥቀሚያ ለምን አናደርገውም? አደራ ከጥንቃቄ ጋር!
አሁን እንኳን ባንችልና ገና ብንሆንም ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ወኔ ለምን አንፈጥርም?

በመፍዘዝ ብቻ ብዙ ከአልጋ ማይወርዱም ትውልዶች በዝተውብናል!

በአላህ እገዛ በዚህ ቻናል ጠንቀቅ እያልን፣ "ላትርፍ ብዬ ልክሰር" ከሚያስብል ነገር እንዲጠብቀን አላህን እየለመንን እላይ ያስቀመጥናቸውን ከ.... የሚጠበቁ ነገሮችን እየተላበስን፦
◈ ሙስሊሞች ሆነው መስመር ሳቱ ላደረጉ
◈ ከኛውም አልፎ ሌላ እምነት ላይ ላሉ ሰዎች የሂዳያ ሰበብ ለመሆን
◈ የደከመው ነቃ እንዲል
በተለያዩ ኢስላማዊና ሌሎች ፕሮግራሞች ለመምጣት አስበናል። ኢንሻአላህ (بحول الله وقوته)

ስንጀምር ግን ወደ መልካም ተጣሪ የሆኑ ሌሎች ሰዎችን መጋፋት! እንዳይሆንብንም እየፈራን ነው፤ እንደው ካልሆነም "ለሌሎች ቀዳሚዎቻችን ማስታወቂያ ሰሪ እንሆናለን" ብለንም ነው የጀመርነው።
بعون الله عز وجل: أكون داعيا إلى الله على بصيرة وآدب، ناصحا لله ولكتابه ولرسوله وللأمة جميعا.

ሁላችንንም አላህ ይቀበለን!!! ነገ ፊት ለፊቱ ቀርበን መድረክ ላይ አውጥቶ ሜዳሊያ እንዲያለብሰን፣ ከካቴናና ሰንሰለት መዳኛ የሚሆነን ስራ ያድርግልን።
ባሳለፍነው ጊዜ ያጓደልነውን ያጠፋነውን አላህ ይቅር ይበለን!!! (عفا الله عما سلف)

✨ ሰዎችን ወደ መልካም ተጣሪዎች ጠቋሚ እየሆንን፣ ወደ መጥፎ ጎታቾች ለሆኑ! ጉንጭና ጀርባ እንዲሰጣቸው እናድርግ።
بارك الله فيكم

        አላህ ያበርታን
     ኢስቲቃማ (ፅናቱን) ይስጠን!
     ✍️w ▰ أبو محمد ኢስማዒል ነጂብ

@metewaweshia
༺❀༻༺❀༻
   𝆺𝅥   𝆺𝅥   𝆺𝅥      𝆺𝅥   𝆺𝅥 𝆺𝅥
@tewhedandsuna

Comments

Be the first to add a comment