የወንጀል ክስ የማቅረቢያ
  (የይርጋ) ግዜ

👇
★ አንድ ግለሰብ በፈፀመው ድርጊት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው ሕጉ በሚያዘው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ የቀረበበት እንደሆነ ብቻ ነው።

★ ሕጉ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ካለፈ የወንጀል ክሱ በይርጋ ስለሚታገድ ድርጊቱን ፈፀመ የተባለው ግለሰብ ክስ ቀርቦበት ሊፈረድበት አይችልም ለበለጠ መረጃ  {የወ/መ/ሕ/ቁ. 226}።

★ ሕግ የሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ (የይርጋ ጊዜ) እንደ ወንጀሉ ዓይነት እና ክብደት የሚለያይ ሲሆን ከባድ ወንጀሎች በ25 ዓመት ይርጋ ሲታገዱ፥ ቀላል ወንጀሎች በ3 ዓመት ይርጋ ይታገዳሉ።

★ የሞት ፍርድ ወይም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የሚጠረጠር ሰው በዚህ ወንጀል በ25 ዓመት ግዜ ውስጥ ክስ ካልቀረበበት ከዛ በኋላ ሊጠየቅ አይችልም የወ / መ/ ሕ/ቁ /_226(U)

★ ይህ የተለመደ _ አሰራር _ በስብእና ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

የሕገ – መንግስቱ አንቀጽ 28 እነዚህን ወንጀሎች በፈፀሙ ሰዎች ላይ የሚቀርብ ክስ በይርጋ እንደማይታገድ በግልጽ ይደነግጋል።

✓ በስብእና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፦ የሰው ዘር ማጥፋትን፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድን፣ በአስገዳጅ ሰውን መሰወርን፣ ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊት መፈፀምን፣ የሚያጠቃልል መሆኑን ይሄው አንቀጽ ይገልጣል። እነዚህ ወንጀሎች የከፋ ሰቆቃን የሚያስከትሉ በመሆናችው ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች የይርጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሕገ መንግስቱ አይፈቅድም፡፡

ሥለዚህ እነዚህን ወንጀሎች የፈጸሙ ሰዎች በሕይወት እስካሉ ድረስ በማንኛውም ግዜ ክስ ሊቀርብባቸው ይችላል።

Comments

Be the first to add a comment