የነገው ግንባታ በዲጂታል መነጽር፦ አዲስ ዘመን፣ አዲስ እይታ!የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከመቼውም ጊዜ በላይ በፈጣን የቴክኖሎጂ ማዕበል ውስጥ እየተናወጠ ይገኛል፤
የድሮው በወረቀትና በኤክሴል የተደገፈ የባህላዊ ግንባታ ዘመን አቅጣጫውን እየቀየረ፣ ቦታውን ለዲጂታል አብዮት እያስረከበ ነው። ዛሬ ላይ ቴክኖሎጂን አቅፈው በዲጂታል የሰሉና የበሰሉ ድርጅቶች፣ ከተራማጅነታቸው ባለፈ በገቢ ረገድ ሌሎቹን እስከ 48% ያስከነዳሉ፤ የትርፍ ህዳጋቸውንም (Net Margin) በ15% ያሳድጋሉ፤
ነገሩ ግን እዚህ ላይ ነው፤ እኛ በዘርፉ ላይ ያለን ሰዎች ራሳችንን ስንመዝን «ቴክኖሎጂና መረጃን በሚገባ እየተጠቀምን ነው» ብለን የምናስብ ብንኖርም፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን 80% የሚሆኑት የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ገና በቴክኖሎጂው መግቢያና መተላለፊያ (beginner level) ላይ ናቸው፤
በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ላይ በምናባዊ እውነታ (Virtual Reality) እና በዲጂታል መንትያ (Digital Twins) የታገዙ ዘመናዊ መፍትሄዎች የግንባታ ቦታዎችን መልክ እየቀየሩት ነው፤
ይህ የለውጥ ማዕበል ደግሞ በውድድር ውስጥ ቀድሞ ለመገኘትና ጥራትን ለማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ምርጫ እየሆነ መጥቷል። በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ለመገኘት እንደ አሁኑ አስደሳችና አስገራሚ ጊዜ የለም! 🚀 የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚቀይሩ 10 ድንቅ ፈጠራዎች 🤖 አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ማሽን ለርኒንግ
ይህማ የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ነው። AI በስራ ቦታዎች ላይ መረጃዎችን በማቀናጀት፣ በመተንበይ (Predictive analytics) እና ስህተትን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ተወዳዳሪ የለውም።
ለምሳሌ እንደ BAM Ireland ያሉ ትልልቅ ድርጅቶች የAutodesk AIን ተጠቅመው በስራ ቦታ ላይ ያለውን ጥራትና ደህንነት 20% ማሻሻል ችለዋል።
📱 የሀብት እና የሰራተኛ አስተዳደር ሶፍትዌር (Resource & Workforce Management)
ሰራተኛንና መኪናን/ቁሳቁስን በተገቢው ቦታና ሰዓት ማሰማራት ትልቅ ራስ ምታት ነው። አሁን ግን እንደ Bridgit Bench እና Riskcast ያሉ ሶፍትዌሮች የትኛው ሰራተኛ የት ቦታ እንዳለ፣ ምን ያህል ወጪ እንደወጣና ወደፊት ምን እንደሚያስፈልግ በስልክ ጭምር በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላሉ።
🖨️ የ3D ህትመት (3D Printing) ቀጣዩ ማዕበል
የ3D ህትመት አሁን ከትርኢትነት አልፎ ወደ ዋናው የገበያ መስመር እየገባ ነው። የግንባታ ቁሳቁስ እጥረት ባለበት ወይም ሩቅ ቦታ ላይ ዲዛይኖችን፣ የፊት ለፊት ገጽታዎችን (Facades) እና ልዩ ልዩ እቃዎችን በጥቂት ሰዓታት ወይም ቀናት ውስጥ ቀርጾ ለማውጣት እጅግ ፍቱን ነው ማባከንን በእጅጉ ይቀንሳል።
🥽 የተራዘመ እውነታ (XR, AR, VR እና Metaverse)
በምናባዊ እውነታ (VR) እና በተቀናጀ እውነታ (AR) አማካኝነት፣ ገና ያልተገነባን ህንጻ ዲጂታል መነጽር አድርጎ በ1፡1 ልኬት ውስጥ ገብቶ ማየትና ስህተቱን ማረም የተለመደ ሆኗል። እንደ Autodesk Workshop XR ያሉ መድረኮች መሃንዲሶች በአካል ሳይገናኙ በሞዴሉ ውስጥ ሆነው እንዲወያዩ ያደርጋሉ።
📡 የሴንሰር መረጃዎች (Sensor Data & IoT) በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ማሽኖች፣ ቁሳቁሶችና ሰራተኞች ላይ ሴንሰር በመግጠም የስራውን ሁኔታ በቅጽበት መከታተል ይቻላል። ማሽኖች ሳይበላሹ አስቀድሞ ለመጠገንና የስራ ቦታ ደህንነትን ለመጠበቅ ሴንሰሮች ወሳኝ ናቸው።
🏢 ዲጂታል መንትያ (Digital Twins)
ይህ ማለት የአንድ ህንጻ ወይም መዋቅር ትክክለኛ የዲጂታል ቅጂ (ኮፒ) መፍጠር ማለት ነው።
ህንጻው ከተገነባ በኋላም እንኳ ውኃ፣ መብራትና ሌሎች አገልግሎቶች እንዴት እየሰሩ እንደሆነ ለመከታተልና የወደፊት የጥገና ወጪን ለማስላት ለአሰሪዎች ትልቅ እፎይታ ነው።
🌐 እውነተኛ የተሳሰረ ግንባታ (Connected Construction)
መረጃዎች በተለያዩ አቃፊዎችና በወረቀት ተበታትነው ሲቀሩ ስራ ይጓተታል። የተሳሰረ ግንባታ ሁሉንም መረጃዎች፣ ዲዛይነሮችና ባለሙያዎች በአንድ የጋራ የዲጂታል መድረክ (Common Data Environment) ላይ በማገናኘት ስራን ቀላልና ግልጽ ያደርገዋል።
📊 የላቁ የግምትና የዋጋ ማውጫ መተግበሪያዎች (Takeoff & Estimating Tools)
በኤክሴል (Excel) መቁጠርና መገመት እየቀረ ነው። አሁን በክላውድ (Cloud) የሚሰሩ እንደ Forma Takeoff እና ProEst ያሉ መተግበሪያዎች የ2D እና 3D ስራዎችን በሰከንዶች ውስጥ ለክተው፣ ትክክለኛ የቁሳቁስና የሰው ኃይል ወጪን በማውጣት ጨረታዎችን በቀላሉ ለማሸነፍ ያግዛሉ።
📐BIM
ከዲዛይን ባለፈ
የህንጻ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM) ቀደም ሲል በቢሮ ውስጥ ለዲዛይን ብቻ ነበር የሚጠቅመው። አሁን ግን ይህ መረጃ ቀጥታ ወደ ግንባታው ሜዳ (Field) በመውረድ በሰራተኞች እጅ መግባት አለበት። ዲዛይኑና ሜዳው ላይ ያለው ስራ ሲጣጣም መደጋገምና መረባበሽ ይቆማል።
⚙️ ሮቦቲክስ
(Robotics)
ድሮኖችና አስቀድመው ተገጣጥመው የሚመጡ ክፍሎች (Prefabrication) አሁን በስፋት እየጠቆሙ ነው።
ሮቦቶች ሰራተኞችን ከአደገኛ ስራዎች በመታደግ፣ ድካምን በመቀነስና ስራን በማፋጠን ረገድ የነገው ተስፋዎች ናቸው።
ባጭሩ፦ ቴክኖሎጂው ስራን ከማቅለል ባለፈ የሰዎችን ህይወት እያሳደገ እና እያቀለለ ነው!@etconp