👉የሳይት ምልከታና የኢንጂነሪንግ ጥያቄ፦

🏛በቅርብ ጊዜ በፒያሳ ገዳም ሰፈር አካባቢ ህንፃዎች ላይ ያየሁት የፋውንዴሽን ስህተት!

🚥በቅርቡ በፒያሳ ገዳም ሰፈር አካባቢ በሚገነቡ ህንፃዎች ላይ የታዘብኳቸውን ሁለት ዋና ዋና የኮንስትራክሽን ስህተቶች አስመልከቶ ከወገኖቼ ለቀረበልኝ ጥያቄ ሙያዊ ምላሽ እንደሚከተለው አዘጋጅቼዋለሁ።

በተለይ በከተማችን እየተስፋፉ ባሉ ግንባታዎች ላይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይደገሙ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ነጥብ ነው።

1️⃣ በአንድ ጊዜ 2 ሜትር selected material ሞልቶ ኮምፓክት ማድረግ ትክክል ነው? ወደፊትስ ህንፃው ላይ ምን ይፈጠራል?
❌ ስህተቱ፦ ይህ አሰራር ፍጹም ስህተትና የኮንስትራክሽን ስታንዳርድን የጣሰ ነው። የኮምፓክሽን መሣሪያዎች (Plate compactor ወይም Rammer) አፈርን በጥራት ማጠባበቅ የሚችሉት ቢበዛ ከ15cm እስከ 20cm (ከፍተኛው 30cm) በሚደርስ ንብርብር (layer) ብቻ ነው። በአንድ ጊዜ 2 ሜትር አፈር ተሞልቶ ከላይ ብቻ ሲረገጥ ከሥር ያለው አፈር ሳይጠብቅ ክፍተት (air voids) እንደያዘ ይቀራል።
⚠️ ወደፊት የሚፈጠረው አደጋ፦
Differential Settlement (እኩል ያልሆነ የመስመጥ አደጋ)፦ ህንፃው ተገንብቶ ሲያልቅና የክብደት ጫና ሲያርፍበት፣ ሳይጠብቅ የቀረውን 2 ሜትር አፈር እየተጫነውና እያሰመጠው ይሄዳል።
የግድግዳና የስትራክቸር ስንጣቂ፦ የመሬት ወለል (Ground Slab) መስመጥ፣ የወለል ሴራሚክስ መነሳት፣ ግድግዳዎችና Beam/Column አካባቢ Structural Cracks እንዲፈጠሩ ያደርጋል።

2️⃣ foundation ውስጥ ውሃ ሳይወጣ አፈር መሙላትና የእንጨት ትራሶች (Formwork) ሳይነሱ መቅበር ምን ችግር ያመጣል?
🌊 ውሃ ሳይወጣ አፈር መሙላት፦
አፈር ከውሃ ጋር ሲደባለቅ ወደ Mud/Slurry (ጭቃ) ይቀየራል። የውሃ መጠኑ ከፍ ስለሚል (Optimum Moisture Content ስላበቃ) ምንም ዓይነት የኮምፓክሽን ጥራት አይኖረውም።

አፈሩ የመሸከም አቅሙን (Bearing Capacity) ያጣል። ውሃው በሂደት ሲደርቅና ሲተን አፈሩ ኮላፕስ በማድረግ ከፍተኛ የመስመጥ አደጋ ያጋጥማል።
መፍትሔው፦ ውሃውን በፓምፕ (Dewatering Pump) ሙሉ በሙሉ አውጥቶ፣ የታችኛውን ጭቃ ካጸዱ በኋላ ብቻ በንብርብር መሙላት ነበረበት።

🪵 የእንጨት ግንድላ፣ ከረባትና ፎርምወርክ ሳይነሱ ከPad ዙሪያ መቀበር፦

የእንጨት መበስበስ (Wood Decay)፦ አፈር ውስጥ የቀረ እንጨት በእርጥበትና በባክቴሪያ ምክንያት ከጊዜ በኋላ ይበሰብሳል።

ትላልቅ ክፍተቶች መፈጠር (Void Creation)፦ እንጨቱ በስብሶ ሲጠፋ በPad ዙሪያ ትላልቅ ባዶ ክፍተቶች ይቀራሉ።

የፋውንዴሽን መንሸራተት፦ የፓድ ፋውንዴሽን ዙሪያውን በደንብ ከተጠጠበቀ አፈር ድጋፍ (Lateral Support) ማግኘት አለበት። እንጨቱ በስብሶ ክፍተት ሲፈጥር ፓዱ የጎንዮሽ ድጋፍ አጥቶ የመንሸራተትና የመናጋት አደጋ ያጋጥመዋል።

💡 ማጠቃለያ፦እነዚህ አይነት የሳይት ቁጥጥር ድክመቶች (Poor Site Supervision) የህንፃውን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥንካሬ አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው፣ በሳይት መሃንዲሱና በሱፐርቫይዘሩ አስቸኳይ የቴክኒክ ማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።

ተመሳሳይ የህንፃ ግንባታ ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካላችሁ ከታች በኮመንት አጋሩኝ!

@etconp

Comments

Be the first to add a comment