⭐️ ሁለቱ የተክቢራ አይነቶች

①) ልቅ የሆነው ተክቢራ (التكبير المطلق)፦

💙ይህ ተክቢራ ዙልሂጃ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዙልሂጃ አስራ ሶስተኛው ቀን ድረስ በየትኛውም አጋጣሚ (በመስጅድ፣ በቤት፣ በሱቅ፣ በመንገድ፣ hiጠዋት፣ ማታ……) ያለምንም ገደብ የሚባል ዚክር ሲሆን። ልክ ዙልሂጃ 13ኛው ቀን ላይ ፀሀይ እንደገባች ይጠናቀቃል።

②
) የተገደበው ተክቢር (التكبير المقيد)፦

💙ይህ ተክቢራ ከሶላት በኋላ የሚባል በሶላት ላይ የተገደበ ተክቢራ ነው። የሚጀመረው የአረፋ ቀን (ዙልሂጃ ዘጠኝ) ሱብሂ እንደተሰገደ ሲሆን ልክ ዙልሂጃ 13ኛ ቀን ላይ አሱር ሶላት ከተሰገደ በኋላ ተብሎ ይጠናቀቃል።

💙ተክቢራ በማለት ላይ እንበርታ።

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ



🌟🔗😊 ᵗᵉʷʰᵉᵈᵃⁿᵈˢᵘⁿᵃ👈🟢
🤩

Comments

Be the first to add a comment