👉አለም አቀፍ ንድፍ ውድድር አሸናፊዎቹ ኑሀሚን እና ሳሙኤል። 💫የ አፍሪካ አርክቴክቶች ማህበር ለኪነህንጻ ለተማሪዎች "Emergency Response for Shelter Design For Displaced People in Africa" በሚል በአፍሪካ ለሚገኙ ተፈናቃይ ሰዎች መጠለያ ያዘጋጀውን አለምአቀፍ የንድፍ ውድድር የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አርክቴክቸር ትምህርት ክፍል አምስተኛ አመት ተማሪ የሆኑት
ኑሀሚን ደሳለኝ እና
ብርሀኑ ተክለማርያም ከምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪዎች አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።
ከምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አንደኛ የወጣ ንድፍ።
የንድፍ ርዕስ "መጠለያን እንደዘር"
"Shelter as a seed"
ER-02-NSA -1ST RUNNER UP - EAST REGION
‹‹አንድ ሰው ቤት መሥራት ሲያቅተው አሥር ሰዎች ግን መንደር መሥራት ይችላሉ›› በሚለው ጥበባዊ አባባል ተነሳስተን የነደፍነው የመጠለያ ንድፋችን ከመጠለያነት አልፎ፣ የበለፀገ ማኅበረሰብን ያጎለብታል ብለን እናስባለን። ንድፋችንን የተፈናቀሉ ሰዎች አካባቢያቸውን በጋራ እንዲቀርጹ ወደሚያስችል የባሕላዊ ገጽታ አሸጋግረነዋል።
እስቲ አስቡት : የነደፍነው አንድ ነጠላ ቤት ብቻ ሳይሆን ለዕድገት የሚሆንን ዘር ነው ያዘጋጀነው። ስደተኞች በታወቁ የአካባቢ ቁሳቁሶች በመጠቀም እና በተፈጥሮ እውቀታቸው እየተመሩ የመጠለያቸው ግንባታ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ።
ይህ ንድፍ መጠለያ ብቻን ሳይሆን ያቀፈው ግለሰቦች ማህበራዊ አስተዋፅዖ በማድረግ ወደሚከበሩበት፣ እና የጋራ ተግባር የሚያብብበት ደማቅ የጋራ ተስፋ የሚሰጥ መልክዓ ምድር መንደር ጭምር ነው። ።
የንድፋችን ፍሬ ነገር የሚከተለው ነው። " በህዝቡ ትብብር የተገነባ ፣ በህዝቡ መንፈስ የተቃኘ ፣ እና በብሩህ የወደፊት ተስፋ የሚያብብ የመንደር ዘር ነው።
ንድፍ ቡድን አባላት።
ኑሀሚን ደሳለኝ እና ብርሀኑ ተክለማርያም
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና ከተማ ፕላን ትምህርት ክፍል።
የ ኢትዮጵያ አርክቴክቸር እና አርባኒዝም ለኑሀሚን እና ብርሀኑ የሚከተለውን ቃለመጠይቅ አድርጎ ነበር። *
ኢአአ። (ኢትዮጵያ አርክቴክቸርና አርባኒዝም) ስለውድድሩ ከየት ነው የሰማችሁት?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ" ስለ ውድድሩ የሰማነው ከ Ethiopian architecture construction and urbanism ቴሌግራም ገጽ ላይ ነበር።
"ኢአአ"። ስንት ቀን ፈጀባችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ " ። የፈጀብን ቀን ከ December 22 አሰከ February 23 ነበር
"ኢአአ"። የስንተኛ አመት ተማሪዎች ናችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ " ። 5 ተኛ አመት ተማሪዎች ነን
"ኢአአ"። እንዴት ሁለታችሁ በግሩፕ ሰራችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ "። ሌላ አነስ ያሉ ታስኮችን አብረን ስንሰራ ስለነበር እናም ስለምንግባባ አብረን ውድድሩን ለመሞከር ወሰንን፣ በተጨማሪም የ software skill ላይ ጥሩ ስለሆንን
"ኢአአ"። ሌላ ከአርባምንጭ የተወዳደሩ ተማሪዎች አሉ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ "። የተመዘገቡ ብዙ ተማሪዎች ነበሩ ውድድሩን እስከመጨረሻ የሄዱ ሌላ 3 ተማሪዎች ነበሩ (አናን ኤልያስ፣ በጸሎት ወንድይፍራው እና ሃይለኢየሱስ ሲሳይ) ይሄ እኛ የምናውቀው ነው።
"ኢአአ"። ሌላ በሀሳብ ያገዛችሁ ሰው አለ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ " አርኪቴክት አዲሱ አዱኛ እና አርኪቴክት ኤሊያስ ጀማል በአጠቃላይ አባ አርኪቴክትስ። እንዲሁም አብሮን በአንድ ክፍል የሚማረው ጉቱ ደጉ በብዙ ሀሳብ ሲረዳን ነበር።
"ኢአአ"። እንዴት አባ አርክቴክት ስ በሀሳብ አገዟችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ" ። Internship እዛ ነበር የወጣነው።
"ኢአአ" ። ማሸነፋችሁን ስትሰሙ ምን ተሰማችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ"። ማሸነፋችን ስንሰማ የነበረው ደስታ ልዩ ነበር ምክንያቱም ከተወሰነ 100 በላይ ተወዳዳሪዎች ነበሩ እንዲሁም ብዙ የደከምንበት ስለነበር ነው።
"ኢአአ" ከዚህ በፊት የዲዛይን ውድድር ተወዳድራችሁ ታቃላችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ"። አዎ በ 120 HOURS it was National Art Museum for Andorra. in this competition we can not get in the finalist list and we are searching for other competition with free entry
"ኢአአ" ። ብርሀኑ ከአርክቴክቸር ምን ደስ ይልሀል?
የምታደንቀው ኢትዮጵያዊ አርክቴክት ማነው? አለምአቀፋዊስ? የምታደንቀው አሁናዊ ህንጻስ?
"ብርሀኑ"። ከአርክቴክቸር እኔ የምወደው ሁሌም አዲስ ነገርን አገኝበታለሁ ሁሌም እየተማርኩበት ነው ምሄደው ሌላው ምንም ነገር እንደሚቻል ያስተማረኝ ነው።
ከኢትዮጵያ የማደንቃቸው አርክቴክቶች ብዙ ቢሆኑም አንድ ለመጥቀስ ያህል አርክቴክት አሃዱ አባይነህ፣ ከውጪ ደግሞ Bjarke Ingels.
የማደንቀው አሁናዊ ህንጻ ደግሞ የ አርክቴክት ዘለቀ በላይ ቦሌ ላይ የነደፈው ህንጻ Nile Source ህንጻ
"ኢአአ" ኑሀሚን ከአርክቴክቸር ምን ደስ ይልሻል?
የምታደንቂው ኢትዮጵያዊ አርክቴክት ማነው? አለምአቀፋዊስ? የምታደንቂው አሁናዊ ህንጻስ?
"ኑሀሚን" ። አርክቴክቸር ለኔ ነግሮችን በብዙ dimension እንዳይ አስችሎኛል፣ የተለያዩ skill እንዳዳብር በብዙ ያደርገናል ፣ ሌላው creative የሆነ mind እንዲኖረን ያደርጋል
ከኢትዮጵያ የማደንቀው አርክቴክት አለበል ደስታ። ከውጪ ደግሞ Zaha Hadid።
የማደንቀው አሁናዊ ህንጻ ደግሞ በአለበል ደስታ የተነደፈው ለ ET 302 memorial ህንጻ።
"ኢአአ" ለሴት አርክቴክቸር ተማሪ የምታስተላልፊው መልዕክት አለ?
"ኑሀሚን"። የጀመራችሁበትን ምክንያት፣ የነበራችሁን ውስጣዊ መነሳሳት እና ፍላጎት ሁሌም አስታውሱ ምክንያቱም ካሰብንበት ለመድረስ ትልቅ ሀይል የሚሰጠን የጀመርንበት ምክንያት ነውና
" ኢአአ" አመሰግናለሁ።
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ" እኛም እናመሰግናለን።
(* ቃለ ምልልሱ በመጋቢት ወር መጨረሻ አካባቢ የተደረገ ነበር)Via ethiopian architecture and urbanism
@etconp