🌱 የአሹራ ቀን🎍የአንድ ቀን ፆም ... የአንድ አመት ወንጀል የሚያስምር !አቡ ቀታዳህ {رضي الله عنه} እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ {ﷺ} ስለ ዓሹራእ ጾም ተጠይቀው እንዲህ አሉ፡-
(صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ، أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ)
«የዓሹራእ ቀን ጾም፣ አላህ ዘንድ ያለፈውን አንድ ዓመት ኃጢአት እንደሚያስምር አስባለሁ።»
📚 [ሙስሊም: 1162]
🍃 ልክ እንደዚው ከአሹራእ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መፆም ይወደዳል
ዐብደ-ል'ሏህ ኢብኑ ዐ-ብ'ባስ {رضي الله عنه} እንዲህ ይላል፡-
«የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የዓሹራእን ቀን ሲጾሙና እንዲጾምም ሲያዙ ሶሐባዎች "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይህንን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል!" አሏቸው፡፡ እሳቸውም እንዲህ አሉ፡-
(فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ إِنْ شَاءَ اللَّهُ صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ!)
"አላህ ካለ፣ መጪው ዓመት ላይ ዘጠነኛውንም ቀን እንጾማለን።"
ኢብኑ ዐ-ብ'ባስ እንዳሉት "የሚቀጥለው ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ሞቱ።"
📚 [ሙስሊም: 1134]
ጁሙዓህ ዘጠነኛው ቀን
ቅዳሜ አሹራእ ነው
╭┈───────ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰┈➤
@ᵗᵉʷʰᵉᵈᵃⁿᵈˢᵘⁿᵃ 🌱] ❞
˓٭˛✿
🌹🍃