መሬት ኖሯችሁ የመገንባት አቅም ከሌላችሁ ከሪል እስቴት ጋር አብሮ ማልማት ማወቅ የሚገቡዎት ነጥቦች
በአሁኑ ወቅት በርካታ የመሬት ባለቤቶች የሚያጋጥማቸው ትልቅ ፈተና መሬት ኖሮ የመገንባት አቅም (ፋይናንስ) ማጣት ነው። ነገር ግን መሬትዎን ሳይሸጡና የቦታ ባለቤትነትዎን ሳያጡ ከፍተኛ ትርፋማ መሆን የሚችሉበት ህጋዊና አስተማማኝ መንገድ አለ እሱም Real Estate Joint Venture (አብሮ ማልማት) ይባላል!
Joint Venture (አብሮ ማልማት) እንዴት ይሰራል?
አሰራሩ ቀላልና ግልጽ ነው።
እርስዎ፦ የመሬት ባለቤት እንደመሆንዎ መጠን መሬትዎን ያቀርባሉ።
አልሚው (Developer)፦ አስፈላጊውን የገንዘብ/የካፒታል አቅም፣ የኢንጂነሪንግ እውቀት እና የግንባታ ሀላፊነት ይወስዳል።
በዚህም መሰረት ዘመናዊ አፓርትመንት ወይም የንግድ ህንፃ በአንድነት በመገንባት፣ የሚገኘውን የቤት/የሱቅ ድርሻ እና ትርፍ አስቀድሞ በተደረገ ስምምነት መሰረት ተደራድረው ይከፋፈላሉ!
በስምምነቱ ወቅት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ 3 ወሳኝ ነጥቦች፦
ስምምነቱ ውጤታማና ከማንኛውም ህጋዊ ስጋት ነፃ እንዲሆን በውል ስምምነቱ (Contract Agreement) ላይ የሚከተሉት ነጥቦች በግልጽ መካተት አለባቸው፦
1. ውል (Joint Venture Contract)፦ የስምምነቱን አጠቃላይ ሁኔታዎች፣ የጊዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ የሚያሳይ አጠቃላይ ህጋዊ ሰነድ ማዘጋጀት እና መስማማት ይኖርባችኾል።
2. ህጋዊ ምዝገባ (Proper Registration)፦ ውሉ በውልና ማስረጃ (document Authentication Agency) ዘንድ በአግባቡ ተመዝግቦ ህጋዊ የጸና አቅም ማግኘቱን ማረጋገጥ ግድ ነዉ።
3. የኃላፊነት ክፍፍል (Clear Responsibilities)፦ የመሬት ባለቤቱ እና የአልሚው መብት፣ ግዴታ እና ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች እንዴት እንደሚሸፈኑ በግልጽ ተለይቶ መስፈር ይኖርበታል።
👉የኮንስትራክሽን ሥራ ውል ከመዘጋጀቱ በፊት ሊታወቁና ሊካተቱ የሚገባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአማርኛ የሚያብራራ ሙያዊ መመሪያ PDF
👷 ሲቪልና ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች
⚖️ የሕግ ባለሙያዎች
🏗️ ተቋራጮችና አማካሪዎች
📋 ፕሮጀክት ማኔጀሮች
🎓 የኮንስትራክሽን ተማሪዎች የሚጠቅም ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት
👇https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a9aa58c0b37b_etconp