የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ከጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚሀ በፊት የነበረውን የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አዋጁን ለማሻሻል የወጡትን ማሻሻያዎችን በመሻር ተግባር ላይ የዋለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 የፍትሐብሔር የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚከተሉት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሠልጣን ይኖራቸዋል፡-
1. የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ ጉዳዮች፤
2. የውጭ ሀገርን ፍርድ ወይም ብይን ማስፀም በሚቀርብ አቤቱታ፤
3. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች፣
4. ከመክሰር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች፤
5. ዓለም አቀፍ የዲኘሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሆኑባቸው ወይም/እና ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተከራካሪ በሆኑበት ጉዳዮች፣
6. የፌደራል መንግሥት አካል ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
7. የፌደራል መንግሥቱን ንብረቶች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፤
8. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች፣ በክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ፣ በክልል እና በድሬዳዋ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ጉዳዮች፣
9. የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣኖችና ሠራተኞች በስራቸዉ ወይም በሃላፊነታቸዉ ምክንያት ኃላፊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣
10. በፌደራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች፣
11. የሚተላፉየገንዘብ ሰነዶች በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
12. በፈጠራ፣ በድርሰትና ሥነ ጥበብ፣ ቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤትነት በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
13. የኢንሹራንስ ውልን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች፣
14. ተገዶ የመያዝ ሕጋዊነትን ለማጣራት የሚቀርብ አቤቱታ፤
15. ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጅ የተሰጣቸው የፍትሀብሔር ዳኝነት ሥልጣን ማለትም በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መታዎቂያ ወረቀት ህግ መሠረት በሚሰጥ ሰነድ ጋር በተያያዘ፣ ከስም ለውጥ፣ ከመጥፋት፣ የፍርድ ክልከላ፣ የባልነት ሚስትነት የአሳዳሪነት የሞግዚትነት ማስረጃ ይሰጠን ጉዳይ፣ የከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድረው ቤት ጋር በተያያዘ በሚነሳ የይዞታ ወይም የባለቤትነት ወይም ሌላ ማንኛውም ክርክር፣ በከተማው ውስጥ ከሚገኝ እዴድር ጋር በተያያዘ የመዲኘት ሥሌጣናቸው እንዯተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በግሇሰቦች መካከሌ የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ፣ ውል፣ እና ብድር ክርክሮች የሚመለከቱ ሆኖ ቀሪ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የሚነሱ የፍትሀብሔር ክርክሮች በ,ፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚዳኙ ይሆናሉ፤
16. በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
የክልል ጉዳይ በክልሉ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ ወይም ከተወሰነ በኋላ ከላይ በቁጥር 8 እና 13 ሥር የተጠቀሱት ተከራካሪ በማንኛወውም ሁኔታ ወደ ክርክሩ ቢገባ እንኳ ጉዳዩ በክልሉ ፍርድ ቤት መታየቱ ይቀጥላል፡፡
ቸር ያሰማን! (28/11/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
Comments
Be the first to add a comment