#ስለታላቁ_የኢትዮጵያህዳሴ_ግድብ
አጠር ያለ ቴክኒካል መረጃ ልስጣችሁ

የኢትዮጲያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካዊያን ኩራትና አዲስ የብርሀን መንገድ የከፈተልን በአለም ላይ ትልቁን ግድብ ሰርተን በማጠናቀቃችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል።

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ከአፍሪካ አንደኛ የሆነ የሀይል ማንጫ ሲሆን ከአለም በሀይል ማመንጨት 3ኛ ነው።

በአለም ከፍተኛ ውሀ የመያዝ አቅሙ እስከዛሬ በሀይል ማመንጨት አንደኛ የተባለው የቻይና three Gorgeous Dam በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ከአስዋን ግድብ በሀይል ማመንጨት 2.5እጥፍ የሚበልጥ ግድብ ነው።

ይህ ግድብ ብሔራዊ ኩራታችን በታሪክ አጋጣሚ አንድ ያደረገን ኢትዮጲያዊያንና አፍሪካዊያንን ያስተደሰተ ያስደመመ ግድብ ነው።

#ታላቁ_ግድባችን_በግንባታ_ወቅት_የነበሩ_አምስት_መሠረታዊ_ተግዳሮቶች

#10ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪት እግዚኦ..

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአለም  በግዝፈቱ በስፋቱ እና በውስብስብ የኢንጂነሪንግ ስራዎች ትልቅ ቢሆንም ግንባታውን ሊያደናቅፉ የሚችሉ በርካታ ቻለንጆች አጋጥመውታል።

ከነዚህ ተግዳሮቶች በመነሳት በርካታ ውስብብ የምህንድስና ጥበብ የተማርንባቸውና ለቀጣይ ትውልድ እና ወደፊት ለሚሰሩ ሜጋ ግንባታ ስራዎች የምንማርባቸው ተጨማሪ የምርምር ስራ የሚሰራበት ጥሩ አጋጣሚ የሆነ ታላቅ ግድብ ነው።

#የነበሩ_ቻለንጆች

1ኛ ከኢንጂነሪግ ቴክኒካል ስራዎች
👉74ቢሊዮን ሜኩ ( 1870km2 ) ስፋት ያለውን ውሀ ለመያዝ የሚያስችል ለዋናው ግድብና ለሌሎች ስትራክቸር ስራዎች ከ10ሚሊዮን ሜኩ ያላነሰ ኮንክሪት ሙሌት ስራ የተሰራ ከአለም በኮንክሪት ሙሌትና በተጠቀምነው የብረት መጠን ከቻይናው 3Gorgeous ቀጥሎ ነው።

የቻይናውን ግድብ ለመስራት 43ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪት  2.7ሚሊዮን ቶን ብረት ተጠቅመዋል

የኛው ግድብ 10ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪትና 175ሺ ቶን ብረት ተጠቅመናል።
ዝርዝሩን ነገ በስልክ ከገባሁ እነግርሃለሁ

በገንዘብ ደረጃ ሁለቱን ስናሰላ
#እንድታውቁት ከፍተኛ ስትሬንግዝ ያለው የኮንክሪት ወጭ በቀላሉ አሁን ባለው ዋጋ =15ሺ ብር ሲሆን =>
10ሚ *  15ሺ = 150ቢሊዮን ብር ሌላውን ተውትና እግዚኦ ከማለት ውጪ ምን ይባላልቢሆን

175ሺ ቶን ብረት ማለት አንድ ቶን 260ሺብር ቢሆን
=> 175ሺ ቶን x 260ሺብር
45.5ቢሊዮን ብር ወጪ ሆኗል


በሁለቱ አይተም ብቻ ወደ 200ቢሊዮን ብር ወጪ ሆኗል።
ሌላውን ሁሉ ትታችሁ ማለት ነው


👉ለግድቡ ስራ ማሳለጫ በርካታ ተያያዥ መሠረተ ልማቶች ለመገንባትና የውሀ መቀልበሻ ግድብ ስራ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግዢ የማሽኖቹ የሰራተኞቹ አረ ብዙ ብዙ

የስራ ቻለንጆች በአጭሩ

👉ተፈጥሮአዊ የመሬቱ አቀማመጥና ከመሬት በታች የተሰሩ በርካታ ውስብስብ ግንባታዎችና የመሬት ውስጥ ጥናት ስራ

👉የሀይል ማንጫ ውስብስብ  የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችና የውስጥ ለውስጥ የዋሻ ግንባታ ስራ

2ኛ #የገንዘብና_የሎጀስትክ አቅርቦት እንዳይኖር አለም አቀፍ ተጽዕኖዎች

3ኛ #አከባቢዊ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ለስራ ምቹ አለመሆን በርካታ ወገኖች ዋጋ መክፈል

4ኛ #አለም_አቀፍ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች መኖር

5ኛ #አለም_አቀፍ_ግዢዎች የኤሌክትሮሜካኒካልና ተያያዥ  የእቃ ግዢ እንዳይከናወን የነበሩ አለም አቀፍ ተጽእኖዎች

እነዚህን አምስት አደገኛ ቻለንጆች አለፈን ግንባታውን አጠናቀን አለምን አስደምመናል እኛም ተደስተናል።

👇👇👇

5ቱ ዝርዝር ጉዳዮች በጥልቀት የተወያየንበትን ሙሉ ፕሮግራም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ሰብስክራይብ ሼር እያደረጋችሁ አድምጡ ።
ማንኛውም ጥያቄዎች ካላችሁ ጻፉልን መልስ እሰጣለሁ ።

መልካም አዲስ አመት

አክባሪያችሁ አቤሴሎም ነኝ
አመሠግናለሁ

https://youtu.be/0BWvynzIC2w?si=m5VdVfPN2oa1ca5a

Comments

Be the first to add a comment