👉የምዝገባ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

💫የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከደረጃ 1-7 ላሉ ሥራ ተቋራጮች ያወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የስራ ተቋራጮች ምዝገባ ከተለያዩ ተሳታፊዎች በቀረቡት አስተያየቶች መሰረት የስራ ተቋራጭ ምዝገባ ቀነ-ገደብ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ፣ በመሆኑም ምዝገባው ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ 5 ተከታታይ ቀናት እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ መራዘሙን ኮርፖሬሽኑ ያሳውቃል።

🚧ስለሆነም፣ ሳትመዘገቡ ለዘገያችሁ ተቋራጮች፣ ይህንን የመጨረሻ ዕድል ተጠቅማችሁ በኦንላይን https://aahdcgeneral.et በመግባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

🏷በምዝገባው ሂደት እና ከምዝገባ በኋላ ለሚኖራችሁ ጥያቂ፣ ቅሬታ https://aahdcgeneral.et/complaints/create ወይም በቴሌግራም https://t.me/aahdcsupport ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

@etconp

Comments

Be the first to add a comment