የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዘመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን የጨረታ ኮሚቴ አሳውቋል፡፡
220 ፕሎቶች በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በተሰናዱበት በዚህ ጨረታ የኦንላይን ሰነድ ሽያጩ ከታህሳስ 25/2018 እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም በተመቻቸው የተቋሙ ድረ-ገፅ ሲሸጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም በተለያየ ምክንያት የጨረታ ሰነድ ላልገዙ አካላት ተጨማሪ እድል ለመስጠትና የተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንዲያግዝ በደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 20 በተደነገገው መሰረት የሰነድ ሽያጩን ከጥር 13/2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
ስለሆነም ፍፁም ፍትሐዊና ግልፅ በሆነው የከተማችን የመሬት ሊዝ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ አካላት የጨረታ ሰነዱን ከጥር 13/2018 እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ የቴሌ ብር አካውንታችሁን ተጠቅማችሁ ሰነዱን ከተቋሙ ድረ-ገፅ (
landlessdocument.aalb.gov.et) በመገዛት እንድትወዳደሩ ቢሮው በድጋሚ ጥሪ እያቀረበ የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 መሆኑን እንገፃለን፡፡
በተጨማሪም ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የጨረታ ቁጥር አ/ቃ/ክ/ከ/27/18 የቦታ ኮድ LDR-AKI-MIX-00014927 የቦታ ስፋት 992 ካሜ ተብሎ የተጠቀሰው 233 ካ.ሜ በሚል የተስተካከለ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ለሚኩራ፣ልደታ እና ኮልፌ ቀራኒዬ ክ/ከተማ በድምሩ 82 ቦታዎች ከጨረታ ተሰርዘዋል ።
የተሰረዙ ቦታዎችን ኮድና ዝርዝር መረጃ ነገ ጥር 09/2018 ታትሞ በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ ይመልከቱ።
@etconp