191_የኮንስትራክሽን_ማዕድን_ፈቃድ_አፈጻጸም_መመሪያ_ቁጥር_191_2018.pdf
283.2 KB
👉በአዲስ አበባ​በኮንስትራክሽን ማዕድን ሥራ ላይ​የተሰማራችሁ አልሚዎችና ተቋራጮች❗️

🏷​
ሰኔ 2018​የወጣውን አዲሱን መመሪያ
​ሰምታችኋል? 


- ​ስራችሁ እንዳይስተጓጎል
​እነዚህን አራት ወሳኝ ነጥቦች
​በፍጥነት እወቁ!

​አንደኛ፡ የፈቃድ ዘመን ገደብ ⏳
​ለጥቁር ድንጋይ ማምረቻ ፈቃድ
​ቢበዛ እስከ አምስት ዓመት፤ 
​ለገረጋንቲ፣ ለአሸዋና ለነጭ ድንጋይ ደግሞ
​እስከ ሁለት ዓመት ብቻ ነው የሚሰጠው። 
​በየዓመቱ መታደስም አለበት! 

​ሁለተኛ፡ ክልክል ቀጠናዎች
​ከቤትዎ ወይም ከኮንስትራክሽን ሳይትዎ አጠገብ ​ማምረት አይችሉም!
​ከመኖሪያ መንደርና ከኢንዱስትሪ ፓርክ
​አምስት መቶ ሜትር፤​ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ​ሃያ አምስት ሜትር፤ከወንዝ ዳርቻ ደግሞ ​ሰላሳ ሜትር ክልል ውስጥ ​ማዕድን ማምረት ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው! 

​ሦስተኛ፡ አዲስ ፈቃድ ለማውጣት 📋
​በአዲሱ አሰራር መሠረት ​ማመልከት ያለባችሁ በፖርታል ብቻ ነው! 
​በሕጋዊ አማካሪ የተና ​የአዋጭነት ጥናት እና
​የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማቅረብ
​ግዴታችሁ ነው! 
​ለደረሰ ጉዳት ማስተካከያ የሚሆን
​የፋይናንስ ዋስትናም ​በባንክ ማስገባት ይጠበቅባችኋል። 
​አራተኛ፡ የድንጋይ መፍጫ ማሽኖች ⚙️
​የድንጋይ መፍጫ ማሽን ​ወይም ባቺንግ ፕላንት ለመትከል ​ፈቃድ የሚሰጠው፤​የማዕድን ማምረት ፈቃድ ላለውና ​በካባው ውስጥ በቂ ቦታ ለሌለው ​ሰው ብቻ ነው! 
​የማሽን መትከያ ፈቃዱም ​ከማምረቻ ፈቃዱ ጋር አብሮ ያበቃል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment