👉ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት (Before Concrete Casting) ሊፈተሹ የሚገቡ 3 ወሳኝ ነገሮች ይዘንላችሁ ቀርበናል

🪧እያንዳንዱ የሳይት ፎርማን፣ መሃንዲስ እና ተቋራጭ ስራ ከመጀመሩ በፊት ማረጋገጥ ያለባቸው ወሳኝ ነጥቦች፦

💫1. የፎርምወርክ ጥንካሬ እና መረጋጋት (Formwork Stability & Alignment)

ኮንክሪት በሚፈስበትና በቫይብሬተር በሚነዝርበት ወቅት የሚፈጠረውን ከፍተኛ ጫና መቋቋም እንዲችል የደገፉት ማገር፣ ማቆሚያዎች (Props) እና ጃኮች ፍጹም ጠንካራ መሆናቸውን ያረጋግጡ።

ፎርምወርኩ ከተንቀሳቀሰ ወይም ከተሰበረ የህንጻውን ቅርጽና ጥራት ከማበላሸቱ ባለፈ ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

💫2. የብረት ሽፋን እና ርቀት (Rebar Cover & Spacing)

ብረቶቹ ከፎርምወርኩ ጋር እንዳይነካኩ እና በኮንክሪት ሙሉ በሙሉ እንዲሸፈኑ ተገቢው የስፔሰር (Spacer blocks/Concrete cover) መኖሩን ያረጋግጡ።

እንዲሁም በንድፉ (Drawing) መሰረት የብረቶቹ ርቀትና ትስስር ትክክል መሆኑን መፈተሽ የህንጻውን የረጅም ጊዜ ጥንካሬ ይወስናል።

💫3. የውሃ እና ሲሚንቶ ጥምርታ (Water-Cement Ratio)

እንደ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት (በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች ወይም በበጋ ወቅት) ኮንክሪት በፍጥነት ሊደርቅና ሊሰነጣጠቅ ስለሚችል የውሃው መጠን ልክ መሆን አለበት::

ውሃ ከመጠን በላይ ከበዛ የኮንክሪቱን ጥንካሬ (Strength) በእጅጉ ይቀንሰዋል፤ ካነሰ ደግሞ ለመስራት አስቸጋሪ (Workability) ይሆናል።

ስለዚህ ትክክለኛውን ድብልቅና የስለምፕ ቴስት (Slump Test) ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment