የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 418
አንድ ሰው የመዝገብ ተካፋይ/ተከራካሪ ባይሆንም በክርክሩ ምክንያት የሱ የሆነ ንብረት እንደመያዣ/ ማስከበሪያ በተከራካሪ ወገኖች ቀርቦበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ንብረት ላይ ያለውንም መብት ለማስጠበቅ የሚያቀርበው አቤቱታም:-
1. መዝገቡ አፈፃፀም እስኪደርስ የዘገየው በበቂ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት
2. በፅሁፍ ሆኖ ፍርዱን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት መቅረብ
3. በንብረቱ ላይ ያለውን የተቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ አብሮ ማያያዝ አለበት።
አቤቱታውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ቢያደርገው አቤት ባዩን በንብረቱ ላይ አዲስ ክስ ከመመስረት አያግደውም።
Comments
Be the first to add a comment