"አንድ መኪና አሸዋ 12ዐ፣ 130 ሺሕ ገብቷል ፥ በቅርቡ 85 ፣ 90 ሺሕ፤ ከዛ በፊት ደግሞ 70 ሺሕ ነበር " - ህንፃ ገንቢዎች
" የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ብር ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል" - ማህበሩከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ ፈታኝ ከሆነው የነዳጅ ችግር ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ግብዓት ዋጋ ከ20 እስከ 40 ሺሕ በላይ መጨመሩን ህንፃ ገንቢዎች እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሃብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከ60 እስከ 70 ሺሕ ብር ይሸጥ የነበረው አንድ መኪና አሸዋ አሁን ከ12ዐ ሺሕ እስከ 130 ሺሕ ብር መግባቱን ቲክቫህ ኢትየያ ከህንፃ ገንቢዎች ገለጻ ተረድቷል።
ከአሸዋ ባሻገር፣ ከወራት በፊት 60 ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረው አንድ መኪና ጠጠር አሁን ከ85 ሺሕ ብር በላይ መሆኑ ታውቋል።
የግንባታ ድንጋይ ደግሞ፣ በሺዎች የሚቆጠር ጭማሪ አሳይቷል። የሲሚንቶ ዋጋም እስከ ሦስት እጥፍ ጨምሯል።
ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሀብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይለማርያም ገቢሳ፣ " በትክክል ጭማሪ አለ። የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል " ብለዋል።
ለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ንረት " የነዳጅም፣ የቢሮ ክራሲም ሰንሰለት " ችግርን እንደ መንስኤ ጠቅሰው፣ እነዚህ ነገሮች ተደምረው አምራች ላልሆኑትም ዋጋ እንዲጨምሩ መንስኤ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።
"ለምሳሌ እኛ አሸዋ እናመርታለን። ከሞጆ እና ከዚያም በታች የሚያመጡም በእንዲህ አይነት ዋጋ መሸጥ ግዴታ ሆኖባቸዋል" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
"ለጭማሪው የተለያዩ ችግሮች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ በትራንስፖርቴሽን መንገድ ላይ ዝም ብለው ሚዛን ይጨምሩብሃል፤ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉሃል። 16 ሜትርኩዩብ መጫን ያለበትን መኪና 10፣ 9 ሜትር ኩዩብ መጫን አለብህ ብለው ያስቸግራሉ" ነው ያሉት።
"በዚህ፣ በዚህ ምክንያት ችግራችን እስከ ታች ድረስ ይወርዳል። ስለዚህ ሳንወድ በግድ ዋጋ እንጨምራለን" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ "የሠራተኛው ደመወዝ መክፈል፤ ነዳጅ መግዛት፣ ለመንግስት ግብር መክፈል አንችልም" ሲሉም ምክንያት ያሉትን አስረድተዋል።
"ነዳጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጣ ጣጣ ነው። አሁን ወደ ዓለም አቀፍ ጉዳይ እየሄደ ነው። የነዳጅ ጉዳይ እኛን ብቻ አይደለም የሚመለከተው" ብለው፣ ነገር ግን በተለያዩ አቅጣጫ የመሰረተ ልማቱን ለማስፋት በተለይ" የጠጠር አምራች ባለሃብቶች ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል ብለን ነው አቤቱታ የምናቀርበው" ብለዋል።
"እነሱን መንግስት ይይልን፤ ከመመሪያ ውጭ አንሆንም፤ ግን በመመሪያ እንዲሆንልን ነው፤ የመንግስት መመሪያ፣ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አዋጅ ይከበር። በዛ መሰረት ሂደን ለመንግስት መክፈል የሚገባንን ዋጋ ከፍለን ወደ ሀገራችን ልማት እንግባ" ነው ያሉት።
Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ
https://t.me/ETCONp@etconpwork