ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,238 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,663 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 37 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2-80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 130 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

98 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል ፣1 ሰው ከአማራ ክልል እና 1 ሰው ከትግራይ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከ ኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።

@tenaET | tena.et/update

1 comment

ብሌን ድንግል ማርያም ልጅ
selam ethiopia