የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም የዕቅድ የአፈጻጸም ሪፖርትና 2019 ዓ.ም. ስትራቴጂክ ዕቅድን በአጠቃላይ የሠራተኛ መድረክ ከፍተኛ የተቋሙ ሀላፊዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት ገመገመ።
የሪፖርቱን ሰነድ የስትራቴጂ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰዋገኝ አታላይ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ የግንባታ ቁጥጥር ማጠናከር፣ የግንባታ ቁሶች ደረጃ ማስተካከል፣ የምርመራና ኦዲት ስራዎችን ማሻሻል እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የሚፈጠሩ ክርክሮችን በውስጥ አቅምና ሁኔታ የመፍታት ስርዓቶችን ማጠናከርን ያካተቱ ዋና የስኬት ነጥቦችን ያሳየ ሆኖ አጠቃላይ የተቋሙ አፈፃፀም 96.71 መሆኑ ተገልጿል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ 39 ግቦችን እና 163 ተግባራትን በማቀድ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማጠናከር ሰፊ ስራዎችን አከናውኗል። ከነዚህ ተግባራት ውስጥ የተገኙ
ዋና ዋና ውጤቶች1,621 ተገልጋዮችን ባሳተፈ የእርካታ ጥናት 98% የአገልግሎት እርካታ ተመዝግቧል።
9,333 ባለሙያዎች፣ 7,398 ኩባንያዎች እና 523 የመንግስት ፕሮጀክቶች ተመዝግበው የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት አግኝተዋል።
300 የሕንፃ፣ 90 የትራንስፖርት እና 60 የውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶች ላይ የቁጥጥርና ክትትል ስራ ተከናውኗል።
46 የሕንፃ እና 25 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው ተረጋግጧል።
84 ፕሮጀክቶች የዲዛይን ግምገማ ተደርጓል።
40 ሀገራዊ የሕንፃ ኮዶችና ስታንዳርዶች ተዘጋጅተው ጸድቀዋል፤ 24 አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ ኮዶች ተካተዋል።
የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ መረጃ ሥርዓት (CRIS) ተጠናቆ ወደ ሙከራ አገልግሎት ገብቷል።
320 በላይ ሰራተኞች በ13 የስልጠና ዘርፎች ስልጠና ወስደዋል።
ማህበራዊ ኃላፊነትን በተመለከተ
ከ3,000 በላይ ችግኞች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተተክለዋል።
ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ለአቅመ ደካሞች የምግብ ድጋፍ እና ለ14 ወላጅ አልባ ህፃናት ቋሚ ድጋፍ ተደርጓል።
በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ በምዝገባ፣በቁጥጥር፣በኮድና ስታንዳርድ ዝግጅት፣በዲጂታል ለውጥ እና በተገልጋይ እርካታ ረገድ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የተቋሙን የቁጥጥር ሥርዓት ማጠናከር መቻሉ ተገልፆል።
በተያያዘም የ2019 ዓ.ም እቅድ የቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በዋናነት የኮንስትራክሽን ዘርፉን ቁጥጥር፣ ጥራት እና የአሰራር ሥርዓት ለማዘመን ያለመ መሆኑ ተገልፆል።
🔖የዕቅዱ ዋና ዋና ነጥቦች
·
የኮንስትራክሽን ኮድ እና ስታንዳርድ: አዳዲስ የህንጻ፣ የውሃ እና የኢነርጂ ኮዶችን ማዘጋጀት፣ ማጽደቅ እና በዲጂታል አማራጮች ተደራሽ ማድረግ።
·
ዲጂታል መረጃ አያያዝ: የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (CRIS) አጠቃቀምን በማጠናከር፣ መረጃዎችን በዳታ ላይ በተመሰረተ መልኩ ለውሳኔ ሰጪነት ማዘጋጀት።
·
ምዝገባ እና ብቃት ማረጋገጫ: ለባለሙያዎችና ለኩባንያዎች የሚሰጠውን የምዝገባ አገልግሎት ቀልጣፋ ማድረግ፣ እንዲሁም የዘርፉን ተዋንያን በአዲስና በነባር ምዝገባ ማካተት።
·
ግጭት አፈታት: የግንባታ ውል አለመግባባቶችን ወደ ፍርድ ቤት ሳይሔዱ በአማራጭ መንገድ የመፍታት አቅምን ማሳደግ።
·
ግንባታ ቁጥጥር እና ኦዲት: በመንግስት በጀት የሚገነቡ የህንጻ፣ የውሃ፣ የኢነርጂ እና የመንገድ ፕሮጀክቶችን በስፋት መከታተል፣ መቆጣጠር እና የኦዲት ስራዎችን ማከናወን።
·
ግብዓት ቁጥጥር: የግንባታ ግብዓቶች አስገዳጅ የጥራት ደረጃዎችን ማሟላታቸውን በገበያ ክትትልና በፋብሪካ ምርመራ ማረጋገጥ።
·
አስተዳደራዊ ድጋፍ: የሰው ኃይል ክህሎትን ማሳደግ፣ የፋይናንስ አስተዳደርን ማዘመን፣ እንዲሁም የሥነ-ምግባር እና የጸረ-ሙስና ስራዎችን ማጠናከር።
·
አካታችነት: በሁሉም የዕቅድ አፈጻጸም ሂደቶች ውስጥ የሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ማረጋገጥ። ይህ ዕቅድ ተቋሙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ጥራትን የጠበቀ እና ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ተቋም እንዲሆን ያለመ ነው።
የቀረበውን ሪፖርትና እቅድ መነሻ በማድረግ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ ግልጸኝነት የሚያስፈልቸው ነጥቦችና ማብራሪያዎች ቀርበዋል በማጠቃለያነትም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር) በቀሪ የበጀት አመቱ ጊዜያት ቀሪ ስራዎች መጠናቀቅ እንደሚባቸው፣ ያለንን አቅም በመጠቀም የ2019 ዓ.ም ስራዎችን ማከናወንና ከስድስት ወራት በኋላ ክለሳ የሚያስፈልቸውን በማየት የሚተገበር መሆኑን፣የሪፎርም ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት በግለሰብ ደረጃ ራስን ማብቃት እንደሚያስፈልግ፣ለሰራተኛው ዲስፕሊን ስነምግባር ወሳኝ በመሆኑ በዲስፕሊን መመራት እንደሚገባና አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሀብሩ ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
@etconp