ክፍል 2
ሀሰተኛ ሰነድ…የቀጠለ
ሀሰተኛ ሰነዶችን የፈጠረ፤ ሰነዶችን ወደ ሐሰተኛነት የለወጠ ወይም ያጠፋ እንደሆነ

-ከ3ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም

-ነገሩ በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ ከ10 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል

አንድ ሰነድ በሚዘጋጅበት ጊዜ ሕጋዊ ዉጤት ያለዉን ወይም ሊኖረዉ የሚችለዉን ማናቸዉንም ሐሰተና ፍሬ ነገር ያስገባ ወይም እንዲገባ ያደረገ እንደሆነ
የአንድን ሰነድ ይዘት በተመለከተ በማሳሳት ሌላ ሰዉ ሌላ ሰነድ/የተለየ ይዘት ያለዉ ሰነድ ላይ የፈረመ መስሎት እንዲሳሳት ካደረገ
ፈቃዱ ባልሆነ ወይም በሌላ ሰዉ ስም ሰነድ የሰጠ ከሆነ
በሀሰት በተዘጋጁ ወይም ወደ ሐሰት በተለወጠ ሰነድ እያወቀ ከተገለገለበት
እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸዉ በጠቅላላዉ ድርጊቱን መፈጸም የሚያስከትሉት የወንጀል ኃላፊነት ወይም ቅጣት ሲሆን በሀሰተኛነት የተፈጠሩት ወይም ወደ ሀሰተኛነት የተለዉጡት ሰነዶች ዓይነት ግን የቅጣቱን ሁኔታ ወይም አይነት ይለዉጡታል ወይም ከፍ ያደርጉታል፡፡
ለምሳሌ የሰነዶቹን ዓይነት መሰረት ያደረጉ ቅጣቶችን ብናይ፡-
በአንድ የመንግስት መዝገብ ፤ በታወቀ ሰነድ ወይም የሕዝብን ጥቅም በሚመለከት ሰነድ ላይ ከሆነ ከ15 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል
በመንግሥት/በሕዝብ መዝገብ በገባ ሰነድ ወይም ሟች እራሱ በእጁ በጻፈዉ ኑዛዜ ላይ ከሆነ
የአገር መከላከያን፤ የመከላከያ ሰራዊት አቋምን፤ ድርጅቱን፤ የሥራ ተግባርን/ጉዳይን በሚመለከት ሰነድ ላይእንደሆነ

ድርጊቱን ፈጻሚ አካል/ግለሰብ በተመለከተ ደግሞ

እነዚህን ከላይ ያነሳናቸዉ መዝገቦች፤ ጽሁፎች የታወቁ ሰነዶች ወይም ሌሎች ሰነዶችን እንዲያዘጋጅ፤ እንዲመዘግብ ፤ እንዲጠብቅ ወይም ከነዚህ ዉስጥ ቅጂዎች እንዲሰጥ ኃላፊነት በተሰጠዉ የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ -ከ5 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት
-የወንጀሉ አፈጻጸም በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ይሆናል

ሕድአት ጌታቸዉ ሕ/ስ/ም/መ/ዳ/ዐቃቤ ሕግ
መጋቢት/2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment