የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሥለ ጦር መሣሪያ ሕግ
ማን፣ ምን መታጠቅ ይችላል?
መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የሕዝብን መብትና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥርን በተመለከተ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈልጎኛል ብሏል።
ረቂቅ አዋጁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጸድቋል።
"ተቆጣጣሪ ተቋም" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና የተሰጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሥሩ ብሔራዊ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሥራ ክፍል አደራጅቶ አዋጁን ያስፈጽማል።
ለመሆኑ ይህ ሕግ ምን ይላል? ማን፣ ምን፣ እንዴት መታጠቅ ይችላል? ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?
የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው?
የጦር መሳሪያ ፍቃድ እና ሁኔታ?
ለግለሰብ የሚፈቀደው አንድ አነስተኛ ወይም አንድ ቀላል የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ለድርጅትም ቢሆን የሚፈቀደው የጦር መሳሪያ አይነት አነስተኛ ወይም ቀላል የጦር መሳሪያ ሲሆን፤ ዝርዝሩ እና የጥይት ብዛት በተቆጣጣሪው ተቋም በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል።
የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተጠየቀበት የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም በሌላ ሰው ስም ፈቃድ ያልወጣበት እና የጦር መሳሪያው ወንጀል ያልተሰራበት መሆን አለበት።
ፍቃድ የሚሰጥባቸው መስፈርቶች
በተቆጣጣሪ ተቋሙ የሚወጣውን ዕድሜ የሚያሟላ፣ ቋሚ አድራሻ እና መተዳደሪያ ገቢ ያለው
ኢትዮጵያዊ የሆነ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ፍቃድ ያለው
1 ከጦር መሳሪያ አያያዝ ጋር ያሉ ሕጎችን ግዴታዎች መወጣት የሚችል
2 ለጦር መሳሪያ ፍቃድና እድሳት አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍል
3 ከሚኖርበት አካባቢ አስተዳደር መልካም ሥነ ምግባር ያለው ለመሆኑ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤ የሚሉ መስፈርቶች ይገኙበታል።
የተከለከሉ ተግባራት
ሀ በዚህ አዋጅ መሰረት ከተፈቀደለት ሰው ውጪ ማንኛውም ሰው፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ እና መለዋወጫዎች ወይም አብረው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሳሪያዎችን፣ ወደ ሀገር ማስገባት እና ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር . . . ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ይገኙበታል።
የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የማይቻልባቸው ሥፍራዎች
1 ሰላማዊ ሰልፍ ወይም አድማ በሚደረግባቸው ሥፍራዎች
2 በምርጫ ሥፍራዎች
ሆቴል፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሙዚየሞች እና ተመሳሳይ በሆኑ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች
3 በትምህርት እና ሃይማኖት ተቋማት ግቢ ውስጥ
3 ሆስፒታል፣ መሥሪያ ቤቶች . . . የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሥፍራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
መሳሪያ ታጥቀው ከላይ ወደ ተጠቀሱት ሥፍራዎች መግባት ካሰቡ በቅድሚያ የጦር መሳሪያውን ለተቋማቱ የጥበቃ ሰራተኞች ማስረከብ ይኖርብዎታል።
mr zee
ምንጭ
የጦር መሠሪያ አዋጅ
በይነ መረብ
Comments
Be the first to add a comment