👉የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ የተራዘመ
መሆኑን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ

ተቋማች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን እና በካፒታል ፕሮጀክት የተገነቡ ንግድ ቤቶችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ 8ኛ ዙር እና 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በተመሳሳይ ቀን በአንድ የጨረታ ሰነድ ማውጣቱ እና የጨረታው 1ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ከግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የሽያጭ ውል ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከሲስተም መቆራረጥ እና ተጫራቾች ካነሱት ከባንክ የገንዘብ ዝውውር መዘግየት አንፃር የባከኑ የስራ ቀናትን ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ 5 ( አምስት ) ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ ቀደም ሲል በተገለፀላችሁ የመዋዋያ ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ በኩል የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በተገለጸው የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈጸም እንድትችሉ ጥሪ የቀረበላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment