Ethio Construction Engineering
👉
በመሰረትና በቤዝመንት ግድግዳ ላይ የሚገጠመው Dimpled / Dimple Board Drainage Membrane ምን ይጠቅማል?
🌟
በምስሉ ላይ በቀይ ቀስቱ የሚታየው በቤዝመንት ወይም በRetaining Wall ውጫዊ ክፍል ላይ የሚገጠመው ባለጉብጥ የፕላስቲክ ሽፋን Dimpled Drainage Membrane / Dimple Board ይባላል።
☄
ይህ ቦርድ በተለይ ከመሬት ውስጥ የሚመጣ ውሃን ለማስወገድ፣ የWaterproofing ሽፋንን ለመጠበቅ እና የቤዝመንት ግድግዳን ከእርጥበት ለመከላከል ይጠቅማል።
▶️
ከታች ከሚገኘው French Drain (Perforated Pipe + Gravel) ጋር በትክክል ሲዋሃድ የሚመጣው ውሃ ወደ ታች በመመራት ከግድግዳው አካባቢ እንዲወገድ ያግዛል።
📌
ዋና ዋና ጥቅሞቹ፦
🔹
Hydrostatic Pressure Relief – የውሃ ጫናን መቀነስ
የDimple Board ጉብጥ ቅርጽ በግድግዳውና በአፈሩ መካከል የውሃ መፍሰሻ ክፍተት ይፈጥራል። በዚህ ክፍተት ውሃው ወደ ታች በመፍሰስ ወደ French Drain Pipe እንዲደርስ ያግዛል።
🔹
Waterproofing Protection – የWaterproofing ሽፋንን መጠበቅ
ከውጭ የሚደረገው የአፈር መሙያና መጠቅጠቂያ (Backfilling & Compaction) ሲከናወን ድንጋይ ወይም ሌሎች ሹል ነገሮች የWaterproofing Membrane እንዳይቀደዱ ተጨማሪ ጥበቃ ይሰጣል።
🔹
Preventing Dampness & Leakage – እርጥበትና የውሃ መፍሰስን መቀነስ
ከመሬት ውስጥ ወይም ከዝናብ የሚመጣ ውሃ ወደ ቤዝመንት ውስጥ እንዳይገባ የDrainage System አካል ሆኖ ይረዳል። ይህም የግድግዳውን እርጥበት ለመቀነስ እና የReinforcement ብረቶችን ከዝገት ለመጠበቅ ያግዛል።
⚠️
በSite ላይ ሲገጠም ሊታዩ የሚገቡ ነጥቦች፦
1️⃣
Dimple Orientation – የጉብጡ አቅጣጫ
Dimple Board ሲገጠም የጉብጥ ክፍሉ በተገቢው አቅጣጫ መዘርጋቱ እና የDrainage ክፍተቱ እንዳይዘጋ መጠበቅ አለበት። የቦርዱ አቅጣጫ ግን እንደ ተጠቀሰው የምርቱ አምራች መመሪያ መሆን አለበት።
2️⃣
Top Termination Bar – የላይኛው ጠርዝ መዝጊያ
የቦርዱ የላይኛው ጫፍ በአፈር ወይም በቆሻሻ እንዳይዘጋ በተገቢው Termination Bar እና በስክሮች በጥንቃቄ መጠበቅ ይገባል።
3️⃣
Integration with French Drain – ከFrench Drain ጋር ማገናኘት
የDimple Board የታችኛው ክፍል ከታች ከተዘረጋው እና በGravel ከተከበበው Perforated Drainage Pipe ጋር በትክክል መገናኘት አለበት።
💡
በአጭሩ፦ Dimple Board ብቻውን Waterproofing አይደለም። ከWaterproofing System ጋር ተያይዞ የDrainage እና የProtection ስራ የሚያግዝ አስፈላጊ ክፍል ነው።
🏗️
በቤዝመንት ወይም Retaining Wall ስራ ላይ Dimple Board ተጠቅመው ያውቃሉ?
@
etconp
Comments
Be the first to add a comment