👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8፣ ለ30 አባወራዎች የሚሆን ባለ G+4 ወለል ህንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄዳቸው ያሉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች አካል የሆነው ይህ መርሃ ግብር፣ የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አንዱ ነው።

ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከሪልስቴት አልሚዎች ማህበር እና ከኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ጋር በትብብር የሚያካሄደው ሲሆን፣ በ90 ቀናት አጠናቆ ለነዋሪዎቹ እንደሚተላለፍ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሕይወት ሳሙኤል ተናግረዋል።

የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር የሱፍ መሃመድ እና
የሪልስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጀበል ጀማል፣ከየዘርፋቸው ተልዕኮ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ የከተማ አስተዳደሩን ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ለማሳካት የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡና ፕሮጀክቱን በ90 ቀናት አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።

ምንጭ:-አሚኔ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment