🏗️Excavation ማለት ብቻ አፈር መቆፈር አይደለም!

🌟በዚህ ፎቶ የምናየው Excavator በመጠቀም የመሬት ቁፋሮ (Excavation) ስራ ነው። ይህ ሂደት በመንገድ፣ በDrainage፣ በFoundation እና በUnderground utilities ግንባታ ውስጥ በጣም ወሳኝ ነው።

📌 ትክክለኛ የExcavation ስራ ሲሰራ ምን መጠንቀቅ አለብን?

🔹 የቁፋሮው ጥልቀትና ስፋት በንድፍ መሠረት መሆን አለበት።
🔹 የመሬቱ አይነትና መረጋጋት መገምገም አለበት።
🔹 ጎኖች እንዳይወድቁ shoring / sloping እንደሚያስፈልግ መወሰን አለበት።
🔹 የውሃ መግባት ካለ በተገቢው መንገድ መቆጣጠር ያስፈልጋል።
🔹 ከቁፋሮው አጠገብ የተቆፈረውን አፈር በጣም ብዙ ማከማቸት በጎን ላይ ተጨማሪ ጭነት ሊፈጥር ይችላል።
🔹 በአካባቢው ያሉ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ ወይም ሌሎች Underground utilities ከመቆፈር በፊት መለየት አለባቸው።

⚠️ አስፈላጊ: Excavation ስራ ቀላል ቢመስልም የመሬት መደርመስ ከፍተኛ የደህንነት አደጋ ስላለው በባለሙያ እቅድና በተገቢው የSafety procedure መሠረት መሰራት አለበት።

“ጥሩ ግንባታ የሚጀምረው በትክክለኛ ቁፋሮ ነው!” 🏗️💪

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment