👉​ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን በተመለከተ የተላለፉ ወሳኝ ውሳኔዎች!

💫​በቅርቡ በእንሳሮ ወረዳ አስተባባሪ አመራሮችና በለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች መካከል በፋብሪካው ወቅታዊ አሠራርና ችግሮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሂዶ የሚከተሉት ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

🚧ዋና ዋና የውሳኔ ነጥቦች፦

​የትራፊክና የትራንስፖርት ፍሰት፦ ሲሚንቶ ጭነው የሚወጡ ተሽከርካሪዎች ከከተማ ውጪ ባለው የ5 ኪ.ሜ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

የወቀሎ ፓርኪንግ ቦታን በማልማት የትራፊክ መጨናነቅን ለመፍታት ስምምነት ተደርሷል።
​የደህንነትና የመግቢያ ሥርዓት፦ ያለ ካርድ ወደ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ መግባት በፍጹም የተከለከለ ነው። የካርድ ሲስተም ከ24 ሰዓት ወደ 48 ሰዓት እንዲሻሻል ተደርጓል።

​የደላሎች መወገድ፦ ህጋዊም ሆነ ህገ-ወጥ ደላሎች ከፋብሪካው ቅጥር ግቢ እንዲወገዱ ጥብቅ ተልዕኮ ተሰጥቷል።

​የደንበኞች አገልግሎት፦ የተደራጁ ወጣቶች ደንበኞችን ያለ እንግልት እንዲያገለግሉና ክፍያዎች እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

​የምርትና ጥሬ ዕቃ ማሻሻያ፦ የሲሚንቶ እጥረትን ለመቅረፍ ከጅቡቲ ወደብ 96,000 ቶን የድንጋይ ከሰል በ300 መኪናዎች እንዲጓጓዝ ተወስኗል፤ እንዲሁም የነበረው 1 መርከብ ወደ 2 ከፍ ብሏል።

​ክትትልና እርምት፦ በፋብሪካው ላይ ማንኛውም ህገ-ወጥ ድርጊት ሲፈጸም የፀጥታ አካላትና የዐቃቢ ህግ አስተማሪ እርምጃ ይወስዳሉ። ምርቱም ለተጠቃሚዎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መሰራጨቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተወስኗል።

​የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አከበረኝ አላማው፣ መንግስትና ማህበረሰቡ ለፋብሪካው መሰረተ ልማት ጥበቃና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

​መረጃው የደረሰን ከእንሳሮ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው

@etconp

Comments

Be the first to add a comment