👉በአንድ የግንባታ ፕሮጀክት Setting Out (ሴቲንግ አውት) በጣም ወሳኝ የመጀመሪያ ስራ ነው።
     ━━━━━━━━━━━━━━
🌟በዚህ ደረጃ የሚደረግ ትንሽ ስህተት በኋላ ኮሎኖች፣ ግድግዳዎች፣ ቢሞች እና ጣሪያዎች ላይ ትልቅ ችግር ሊያመጣ ይችላል።

1. ከሴቲንግ አውት በፊት የሚደረጉ ዝግጅቶች

✤የApproved Site Plan እና Structural Drawing በትክክል ማጥናት።
✤የመሬት ወሰን (Boundary) በሕጋዊ ሰነድ ማረጋገጥ።
✤የBenchmark (BM) መፈለግ ወይም መመስረት።
✤የGrid Line እና Column Center መጠኖችን ማረጋገጥ።
✤መሳሪያዎች (Total Station፣ Theodolite፣ Auto Level፣ Tape) ካሊብሬት መሆናቸውን ማረጋገጥ።

2. ሴቲንግ አውት ሲደረግ የሚወሰዱ ጥንቃቄዎች

✤የGrid Line ርቀቶችን ሁለት ጊዜ መለካት።
✤የColumn Center ቦታዎችን ከድሮዊንግ ጋር ማነጻጸር።
✤የ90° ማዕዘን ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ።
✤ዲያጎናል (Diagonal) መለካት፤ ሁለቱ ዲያጎናሎች እኩል ከሆኑ ሌይአውቱ ትክክል ነው።
✤የLevel ልዩነትን በAuto Level መመርመር።
✤የOffset Peg እና Profile Board (Batter Board) ከቁፋሮ ውጭ ማስቀመጥ እንዳይነኩ።
✤ሁሉንም መለኪያ ከመቆፈር በፊት በኮንሰልታንት ወይም በሳይት ኢንጂነር ማረጋገጥ።

3. የሴቲንግ አውት ዘዴዎች

✤Total Station – በጣም ትክክለኛ እና ዘመናዊ ዘዴ፤ ለአብዛኛው ፕሮጀክት ይመከራል።
✤Theodolite + Tape – አንግልና ርቀት በመለካት የሚሰራ።
✤Tape Measure (3-4-5 Method) – ለትንንሽ ሕንፃዎች ቀላል ዘዴ። 3m፣ 4m እና 5m በመጠቀም 90° ይፈጥራል።
✤GPS – ለትልልቅ የመሬት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ኮኦርዲኔት ለማስቀመጥ ይጠቅማል።

4. ምርጥ አሰራር (Best Practice)

✤አንድ ጊዜ ብቻ አትለኩ፤ "Measure twice, set out once."
✤ከቁፋሮ በፊት ኮሎን ሴንተሮችን፣ Grid Lines እና Levels በድጋሚ ያረጋግጡ።
✤የSetting Out መዝገብ (Field Book) ይያዙ፣ ሁሉንም መለኪያ ይመዝግቡ።
✤የሴቲንግ አውት ስራ በትክክል ከተሰራ፣ ፋውንዴሽን፣ ኮሎኖች፣ ቢሞች እና ሙሉ ሕንፃው በዲዛይኑ መሠረት ይገነባሉ።

✅የSetting Out ደረጃ በደረጃ

1. የድሮዊንግ ምርመራ

Architectural እና Structural Drawing ያወዳድሩ።
Grid Line፣ Column Center፣ Foundation Size እና Setback ያረጋግጡ።
ሁሉም መጠኖች ተመሳሳይ መሆናቸውን ያረጋግጡ።

2. Benchmark (BM) ማስቀመጥ

በማይነካ ቦታ ቋሚ Benchmark ይመስርቱ።
የፕሮጀክቱን ±0.00 ደረጃ ከዚህ ይወስኑ።

3. Baseline መፍጠር

አንድ ቀጥተኛ መስመር (Baseline) ይምረጡ።
ከዚያ የቀሩትን Grid Line ይለኩ።

4. Grid Line ማስቀመጥ

Total Station ካለ እሱን ይጠቀሙ።
ከሌለ በTape እና 3-4-5 Method 90° ያረጋግጡ።
ሁሉንም Grid Line በPeg ያመልክቱ።

5. Profile Board (Batter Board) መትከል

ከFoundation ውጭ 1–2 ሜትር ርቀት ላይ ይትከሉ።
ቁፋሮ ቢደረግም የGrid Line እንዳይጠፋ ይረዳል።

6. String Line መሳብ

በProfile Board ላይ ገመድ ይሳቡ።
የገመዱ መገናኛ ቦታ የColumn Center ይሆናል።

7. የኮንሰልታንት ማረጋገጫ

ከሳይት ኢንጂነር ወይም ከኮንሰልታንት ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ ቁፋሮ ይጀምሩ።

━━━━━━━━━━━━━━
@etconp

Comments

Be the first to add a comment