#ጳጉሜ_በህግ_እይታ

የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1858 እና 1859
🏛 ሰ/መ/ቁ. 96458 ቅጽ 16፣ ፍ/ህ/ቁ. 1860(3)
✍️  ይርጋ ማለት የመብት ጥያቄ ጊዜ በማለፉ ቀሪ የሚሆንበት እና በአንፃሩ መብት ላልነበረው የሚያጎናፅፍ ነው፡፡

👉  ጳጉሜ እንደ አስራ ሦስተኛ ወር የማትቆጠር መሆኑ የሚታወቅና የሀገራችን የአንድ አመት ጊዜ 12 ወራቶች ከሆኑ ከዚህ አቆጣጠር ውጭ ያሉት ቀናት በአሰሪና ሰራተኛው መካከል መብትም ሆነ ግዴታ ሊፈጥሩ አይገባም፡፡

👉 ጳጉሜ ሰራተኛው ሥራም ላይ ቢሆኑ የሚሰጣቸው ጥቅም ወይም በመብት ደረጃ የሚጠይቁትም ክፍያ የለም፡፡እንግዲህ እንደወር የማይቆጠረው ‘ጊዜ’ ለቀረበው ከውል መቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚነሣውን የክፍያ ጥያቄ ጳጉሜ በይርጋ አቆጣጠር በማስገባት ተሰልቶ የሰራተኛውን መብት ሊያጣብብ አይገባውም።

👉 ህጉ የይርጋ ጊዜውን በወር ወይም ወራት ከወሰነ ጊዜው የሚቆጠረው በጳጉሜ ውስጥ ያሉት ቀናት ታሳቢ ሳይደረጉ ነው፡፡ በፍትሐብሔር ህጉ ቁጥር 1860(3) በተመለከተው የጊዜ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ጳጉሜ እንደወር አይቆጠርም፡፡ ጳጉሜ እንደ አስራ ሦስተኛ ወር የማትቆጠር መሆኑ ከታወቀና የሀገራችን የአንድ አመት ጊዜ 12 ወራቶች ከሆኑ ከዚህ አቆጣጠር ውጭ ያሉት ቀናት በተዋዋይ ወገኖች መካከል መብትም ሆነ ግዴታ ሊፈጥሩ አይገባም፡፡

👉 ጳጉሜ በህግ እይታ ወር አይደለችም ስለዚህ  ወርን መሰረት አድርጎ የሚደረጉ ውሎች፣ ስምምነቶች ፣ ግብይቶች ፣ ወዘተ አይመለከቷትም ( መብትና ግዴታ ልትፈጥር አትችልም) ። ደመወዝ ፣የቤት ኪራይ፣ ብድር ወዘተ ወርን መሰረት አድርገው የተፈፀሙ ነገሮች በጳጉማ በተግባር ላይ አይውሉም ። በተቃራኒው! በቀን(ኖች) እና በሳምንት (ቶች) የተወሰኑ ከሆኑ በጳጉሜም ቢሆን በተግባር ላይ ይውላሉ።

Comments

Be the first to add a comment