👉ለማሽነሪ አከራዮች

በእጅዎ የሚገኙትን የማሽነሪ መሳሪያዎች ከማከራየትዎ በፊት የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት ውስጥ ቢያስገቡ ዋጋን ለመተመን፣ ደንበኛ ለማፍራት እና የገበያ ዋጋን ለመገመት ይረዳዎታል፡፡

💫የአካባቢውን የኪራይ ዋጋ ማወቅ

እርስዎ በሚያከራዩበት አካባቢ ተመሳሳይ ማሽነሪዎችን የሚያከራዩ ሰዎችን በምን ያህል ዋጋ እንደሚያከራዩ በመጠየቅ የራስዎትን ዋጋ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡

💫የማሽነሪዎችን ዘመናዊነት ማረጋገጥ

የተከራዮችን ቀልብ ለመሳብ፣ የሚያከራዩት ማሽን ከተመሳሳይ ማሽኖች ጋር ያለውን ልዩነት፣ ዘመናዊነት፣ ቅልጥፍ፣ የሚጠቀመውን ቴክኖሎጂ እንዲሁም ብቃት ማወቅ ወሳኝ ነው፡፡

💫ጊዜው በአግባቡ መረዳት

የማንኛውም ዕቃ ዋጋ የሚወስነው በወቅቱ ባለው ፍላጎትና ኢኮኖሚ ሁኔታ ነው፡፡ በአንዳንድ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ተገልጋዮች መከራየትን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ማሽን ከመከራየት ይልቅ መግዛቱ የተሻለ አማራጭ ሊሆንላቸው ይችላል፡፡ ከዚህ በመነሳት ለመከራየት የሚጠይቁት ገንዘብ እነዚህ ሁለት ኢኮኖሚያዊ ውጣ ውረዶች ከግምት ያስገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

💫ለቦታና ላለው ነባራዊ ሁኔታ ያለው ተመራጭነት

የእርስዎ ማሽነሪ አሁን ሊከራይ በተዘጋጀበት ቦታና ባለው ነባራዊ ሁኔታ ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑን ካወቁ፣ ከፍ ባለ ዋጋ የማከራየት ዕድል ይፈጥርልዎታል፡፡

💫ሳያከራዩ ማቆየት ወይም በአነስተኛ ዋጋ ማከራየት

በፈለጉት ዋጋ የሚከራይ ባለመኖሩ የተነሳ፣ ማሽኖቹን ሳያከራዩ ማስቀመጥ በሚያገኙት ትርፍ ላይ ገደብ ሊያስቀምጥ የመቻሉ ሁኔታ ከፍተኛ ነው፤ ማሽን የሚያከራዩ ከፍተኛ ባለሃብቶች ሳያከራዩ ለማቆየት ከፍተኛ ትዕግስት የተላበሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ የራስዎትን አቅም በመመዘን ባለማከራየትዎ የሚደርስቦትን ጫና በመረዳት በአነስተኛ ዋጋ ማከራየት ወይም መተው ምርጫዎ ነው!

@etconp

Comments

Be the first to add a comment