👉ሒልተን በ55 ሚሊዮን ዶላር ሊስፋፋ ነው

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ያለውን የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ለማስፋፋትና ለማጠናከር ያለመ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሠረት በነባሩ የሒልተን አዲስ አበባ ሆቴል ግቢ ውስጥ ባለ 150 ክፍሎች ያሉት «ሂልተን ጋርደን ኢን» ሆቴል እና ዘመናዊ የዌልነስ ማዕከል ይገነባል።

በጥቅሉ 55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተመደበለት ይህ ፕሮጀክት የድርጅቱን ነባር ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የእንግዳ ተቀባይነት አገልግሎቶችን ለማስፋፋት የተወጠነ ነው።

በተጨማሪም አዲስ አበባ እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2027 ለምታስተናግደው የዓለም አቀፉ የኮፕ32 (COP32) የአየር ንብረት ጉባኤ አስቀድሞ ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድና የቱሪዝም ማዕከልነቷን የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

የዚህ አዲስ ሆቴል የዲዛይን እና ግንባታ ሥራ በኢልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ የሚከናወን ሲሆን፣ ዚያስ አርክቴክቸር ኤንድ ኢንጂነሪንግ ደግሞ የፕሮጀክቱ አማካሪ ሆኖ ተመድቧል።

ሙሉ ግንባታው ከኮፕ32 ጉባኤ አስቀድሞ እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2027 ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment