👉በመጪው ዓመት ከ1 ሺህ 600 በላይ ቤቶች ተጠናቅቀው ለአቅመ ደካሞች ይተላለፋሉ

💫በመጪው አዲስ ዓመት 1 ሺህ 661 ቤቶች ተጠናቅቀው ለአቅመ ደካሞች የሚተላለፉ መሆኑን የአዲስ አበባ የበጎ ፍቃድ አገልግሎትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

🚧በኮሚሽኑ የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ሙሉጌታ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንድ ሺህ 661 ቤቶች በግንባታ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ በመጪው አዲስ ዓመት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ይሆናል፡፡

⏺በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 2 ነጥብ ሁለት ሚሊየን በጎ ፍቃደኞችን በድግግሞሽ ተሳታፊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

⏺በክረምቱ እየተከናወኑ በሚገኙ የበጎ ፍቃድ ተገባራት ከ805 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ከፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

⏺በጎ ፍቃደኞች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን አዋጥተው አስተዋጾኣቻውን እንዲያበረክቱ ኮሚሽኑ 15 ዋና ዋና ፕሮግራሞችና 19 ንዑስ ፕሮግራሞችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ግልጸዋል፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment