‎👉Site Setting Out ልየታ ላይ ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች

‎🏗በግንባታ ሼል ከቦታ መጥረግ ቀጥሎ የሚሰራው ሼል የግንባታ መስመሮችን (Axis) እና የስትራክቸር መሰረታዊ ማዕከላዊ ነጥቦችን (Center of structures/column) መለየት ነው።

ይህ ሥራ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት የሚባል ሲሆን መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች፦

‎1) የተዘጋጀ ቦታ መሆኑን ፦ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት (Site Setting Out) ከመከናወኑ በፊት ሲባጎ የሚወጠሩባቸው ችካሎች ወይም የጂፒኤስ (GPS) መሳሪያ የሚያመለክትባቸው ነጥቦች ከፍታ (Elevation of setting out strings) በውል እንዲታወቅ እና ተፈጥሯዊ የላይኛው የመሬት ክፍል ያለበት ክፍታ (Top Surface /Elevation/ of Original Ground Level) የተለየ መሆን ስላለበት የግንባታ ቦታ ጠረጋ በሚገባ የተከናወነ መሆኑን እና ተፈጥሯዊ የመሬት የላይኛው ክፍል የተደረሰበት መሆኑ ማረጋገጥ አለበት።
‎
‎2) መሪ ንድፍ  (site plan) መኖሩን እና በዚያ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን፦ መሐንዲሱ አንድ ሕንጻ የሚያርፍባቸውን መሰረታዊ ነጥቦት (Axis & Center) ልየታ በሚከናወንበት ሰዓት ሕጋዊ የሆነ መሪ የቦታ ንድፍ (site plan) ያለው እና በግንባታ ቦታው ላይ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
‎
‎3) ዋና ዋና ፍርግርግ መስመሮች (main grid/Axis/ lines)፦ የግንባታው ሁለትዮች አቅጣጫዎች (X-axis and Y-axis) የሚገናኙበትን የሚያመለክቱ ፍርግርግ መስመሮች መኖራቸውን፣ ከፍታ ልዩነት አለመኖሩን (water level) ማረገግጥ አለበት። በዚህም መሰረት እርስ በእርሳቸው የሚገናኙበት አንግል እና አንዱ ከሌላው ያለው ማዕከላዊ ርቀት (centerline dimensions) በስትራክቸራል የመሰረት አቀማመጥ ዲዛይኑ (Structural foundation layout) ላይ በተመለከተው ልኬት መሰረት ምንም አይነት የልኬት ክፍተት የሌለባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት።
‎
‎4) የስትራክቸር ክፍሎች መገኛ (Location of Structural Elements):- በዋናነት እያንዳንዱ የስትራክቸሩ ምሰሶዎች/ቋሚ አምዶች ማዕከላዊ ነጥብ(Columns centerline)፣ እና የስትራክቸሩ ምሰሶዎች የሚያርፉባቸውን አካላይ ነጥቦት (Coordinate points)፣ የምሰሶ ጫማ ስፋት (Footings coverage area) የሚያመለክት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
‎
‎5) የአጥር ሼል (fencing or barbed)፦ በሚቆፈረው የመሬት ክፍል ውስጥ ማየት የተሳናቸው፣ ሕጻናት፣ በጨለማ የሚጓዙ መንገደኞች፣ እንስሳት እንዳይወድቁና አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስ፤ በተጨማሪም በግንባታው ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደ ሚስማር፣ ብረት፣ እንጨት አይነት ግብአቶች እንቅፋት በመሆን ጉዳት እንዳያስከትሉ፣ ወይም በግንባታ ቦታው ውስጥ ያሉ የግንባታ ግብአቶች፣ ማሽኖች፣ እቃዎች፣ እና ሌሎች ንብረቶች እንዳይዘረፉ ለመከላከል የግንባታ ቦታው የታጠረ ወይም የተከለለ መሆኑ ማረጋገጥም የክትትል መሐንዲሱ ሼል ነው።

‎⭐️የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment