🌱 ጥብቅ የሳይበር ደህንነት ማስጠንቀቂያ
‼=========================
(ቴሌግራም ላይ የተሰማራው አደገኛው Botnet እና የብልግና ሊንኮች!)
||
✿ ሰሞኑን በቴሌግራም መድረክ ላይ እጅግ አደገኛ እና የተራቀቀ የአካውንት ጠለፋ (Account Takeover) ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ጥቃት እንዴት እንደሚሰራ እና እያንዳንዳችንን እንዴት አደጋ ላይ እየጣለን እንደሆነ እውነታውን ላካፍላችሁ።
¹/ ጥቃቱ እንዴት ይሰራል?
•┈┈ አጥቂዎቹ (Hackers) የሚጠቀሙት "Phishing Attack" እና አውቶማቲክ የሆኑ የቴሌግራም Botnets በማጣመር ነው። ስልቱ እንዲህ ነው፦
• ማጥመጃው (The Bait)፡ የሰውን ልጅ የስነ-ልቦና ድክመት (Social Engineering) ለመጠቀም ሲሉ፣ በጣም ፀያፍ የሆኑ (የብልግና) ምስሎችን ወይም ቪዲዮዎችን ይልካሉ። ከስሩም "ሙሉውን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ" የሚል ማባበያ (Malicious Link) ያስቀምጣሉ።
• የታመነ ምንጭ (Trusted Sender)፡
ይህ ሊንክ የሚመጣው ከማታውቁት ሰው ብቻ አይደለም! አካውንቱ በጠላፊዎች (Hackers) ቁጥጥር ስር ከዋለ የቅርብ ጓደኛችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ፣ ወይም አብሮ አደጋችሁ ስም ሊመጣ ይችላል።
²/ ሊንኩን ስትነኩት ምን ይፈጠራል?
•┈┈ ሊንኩን ክሊክ ባደረጋችሁበት ቅጽበት In a fraction of a second ሁለት ነገሮች ይፈጠራሉ፦
1】 የቴሌግራም አካውንታችሁን የመቆጣጠር መብት (Access Token/Session Hijacking) ለአጥቂዎቹ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
2】 በስተጀርባ የተጻፈው (Automated Script/Bot) ወዲያውኑ የእናንተን አካውንት በመጠቀም Contacts ላይ ለሚገኙ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እና አባል ለሆናችሁባቸው ግሩፖች በሙሉ ያንኑ የብልግና ምስል እና ቫይረስ በእናንተ ስም ያሰራጫል። አንዴ ከተጠለፈ አካውንታችሁን መልሶ ለማግኘት (Account Recovery) እጅግ ፈታኝ ይሆናል።
3】 ከሳይበር አደጋው ባሻገር፣ ይህ ነገር እጅግ ከባድ የሞራል እና የኃይማኖት ቀውስ እያስከተለ ነው። አንዳንዶች በስሜት (Curiosity) አሊያም በድንቁርና ሊንኩን ይከፍቱና፤ ለራሳቸውም ሐራም እያዩ፣ በራሳቸው አካውንት ምክንያት ደግሞ ያንኑ የብልግና ምስል ለብዙ መቶ ንጹሃን ሰዎች (ለቤተሰብ፣ ለኡስታዞች፣ ለወንድም እህቶች) ልከው በቅጽበት ሰውየውንም ሐራም እንዲያይ ያስገድዱታል።
▢ በዲናችን አስተምህሮ፡- "ወንጀልን (ፋሒሻን) ማሰራጨት እና ሰዎችን ወደ ሐራም መጋበዝ ከባድ ቅጣት አለው!" ዛሬ በእናንተ ድክመትና ስግብግብነት የላካችሁት ሊንክ የብዙ ወጣቶችን አዕምሮ ሊበክል፣ ስነ-ልቦና ሊጎዳ እና ትውልድ ሊያበላሽ ይችላል።
★ መፍትሄወ፦
• አትንኩ! ከማንም ይምጣ ከማን (ከጓደኛም፣ ከዘመድም፣ ከባለቤታችሁም)፣ ፀያፍ ምስል ወይም የሚያጠራጥር ሊንክ (Link) ከተላከላችሁ በፍጹም አትንኩት ወዲያውኑ delete አድርጉት።
• Two-Step Verification አብሩ: የቴሌግራም ሴኩሪቲያችሁን ለማጠናከር፣ Setting > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ በመግባት Password አድርጉበት! ይህ አካውንታችሁ በቀላሉ እንዳይጠለፍ ትልቅ ግድግዳ (Layer of security) ይፈጥራል።
• ያላወቃችሁትን Session አጥፉ: ወደ Setting > Devices ገብታችሁ እናንተ ከምትጠቀሙበት ስልክ ውጪ የሚታይ ሌላ የገባ (Active) አካውንት ካለ "Terminate all other sessions" በማለት ወዲያውኑ አጥፉት።
• የሳይበር ደህንነታችንን መጠበቅ ዲናችንንም፣ ክብራችንንም၊ ማህበራዊ ግንኙነታችንንም መጠበቅ ነው። የብዙዎች ህይወት፣ ትዳር እና ክብር በዚህ አደገኛ ጥቃት ምክንያት እየፈረሰ ነው።
እባካችሁ ንቁ! ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎች ጥንቃቄ አድርጉ!
(ይህን ማስጠንቀቂያ Share በማድረግ ወዳጅ ዘመድዎን ከዚህ አደገኛ የሳይበር እና የሞራል ወጥመድ ይታደጉ!)
||
© STEM with Murad
🌱 @TewhedandSuna