ፓን አፍሪካን ቢየናሌ 2026
ናይሮቢ ኬንያ
ፓን አፍሪካ ቢየናሌ በናይሮቢ ከ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓም እስከ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓም ድረስ ይካሄዳል።
ይህ የፓን አፍሪካን ቢየናሌ ከሁሉም የአፍሪካ አገሮች የተወከሉ የኪነህንጻ አማካሪ ባለሙያዎች ስራቸውን የሚያቀርቡበት መርሀ ግብር ሲኖረው ኢትዮጵያ በ ራስ አርክቴክትስ ተወክላለች።
የባለሙያ ምርጫው በቢየናሌ አዘጋጆቹ የተወሰነ ሲሆን፣ እንደ ቬኒስ ቢየናሌ አገራት ውድ ብር ከፍለውበት የሚዘጋጅ መርሀግብር አይደለም።
ማንኛውም ሰው በነጻ መካፈል የሚችል ሲሆን የአገራችን ህንጻ ነዳፊዎች እና አማካሪዎች በአካል ተገኝተው ልምድ ቢለዋወጡ እና አህጉራዊ አድማሳቸውን ቢያሰፉ ይመከራል።
ሙሉ መረጃውን ከተያያዘው ኦፊሴላዊ ድረገጽ ላይ መውሰድ ይቻላል።
https://www.panafricanbiennale.org/@etconp