👉ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ (አስቸኳይ)

ቀጣሪ ድርጅት፦ ፕሮቴክ ኮንስትራክሽን (Protech Construction)

የስራ መደብ፦ ዳታ ኮሌክተር (Data Collector)

ተፈላጊ ብዛት፦ 2 (ሁለት)

የስራ ቦታ፦ አዲስ አበባ (በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች)

የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት

ደመወዝ፦ 10,000.00 ብር (የተጣራ / Net Salary)

የትምህርት ደረጃ፦ በሲቪል መሃንዲስነት (Civil Engineering) ወይም በተያያዥ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የ2025/2026 (የ2017/2018 ዓ.ም) ተመርቂ/ምሩቅ

የስራ ልምድ፦ 0 ዓመት (አዲስ ምሩቅ / Fresh Graduate)

የስራው መግለጫ (Job Description)፦
በዚህ የስራ መደብ ላይ የሚቀጠረው ባለሙያ በግንባታ ሳይት ላይ በየቀኑ በተግባር የተከናወኑ የስራ መጠን ልኬቶችን (Executed Quantities) በጥንቃቄ የመሰብሰብ፣ የማስላት እና የመመዝገብ ኃላፊነት አለበት። የተሰበሰቡትን መረጃዎች በማደራጀት ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን (Weekly & Monthly Reports) ያዘጋጃል። በተጨማሪም በሳይት ደረጃ የሚወጡ ወጪዎችን፣ የጥሬ ዕቃዎችን እና የሰው ኃይል አጠቃቀም በመከታተል የበጀትና የወጪ ሚዛንን (Cost Balancing) የመጠበቅና የመቆጣጠር ስራ ያከናውናል።

የማመልከቻ መመሪያ፦ ስራው አስቸኳይ (Urgent) በመሆኑ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የህይወት ታሪካችሁን (CV) በቴሌግራም አድራሻችን @my162129 በመላክ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

@etconp

1 comment

Z+Bêñêfìç 🐍
Hi