🌱 በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በኩል ፈትዋ መውሰድ ይቻላል?

​መልሱ፦ በሸሪዓዊ ፈትዋዎች ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መመካት የተከለከለ (ሀራም) ነው።

ይህ የሆነው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

• ​አንደኛ፦ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ወደ እውቀት ባለቤቶች እንድንመለስ አዞናል። እንዲህም ብሏል፦ “የማታውቁ ከሆናችሁም የእውቀትን ባለቤቶች (አህለ-ዚክር) ጠይቁ።” ትእዛዙ እውቀት ያላቸው ሰዎች ላይ እንድንመለስ እንጂ ወደ ድረ-ገጾች እንድንመለስ አይደለም።

•​ሁለተኛ፦ የምንጩ አለመታወቅ (ጅሃለቱል መስደር)። አሁን መረጃ ይሰጥሃል፤ ግን ይህን መረጃ ከየት ነው ያመጣው? የዚህ መረጃ ምንጭ ምንድነው? ከመናፍቃን (ሙብተዲዓ) ድረ-ገጽ ነው? ወይስ ከመናፍቅ ሼህ? ወይስ ከአህለ-ሱና ወል-ጀመዓ ሼህ? የመረጃው ምንጭ አይታወቅም፤ ታዲያ እንዴት ሸሪዓዊ ፈትዋ ከእሱ ትወስዳለህ?

•​ሶስተኛ፦ የፈትዋ ብቃት (አህሊያ)፣ ነባራዊ ሁኔታን የመረዳት እና የጠያቂውን ሁኔታ የማወቅ ጉድለት ነው። አንድ አሊም (ሊቅ) የጠያቂውን ሁኔታ ማወቅ አለበት፣ ነባራዊ ሁኔታውንም ማወቅ አለበት። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ይህንን እንዴት ሊያውቅ ይችላል?

•​አራተኛ፦ በሙከራዎች እንደተረጋገጠው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አንዳንዴ፣ ይልቁንም ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ መረጃዎችን ይሰጣል።

ሼሁ ያጋጠማቸውን ገጠመኝ ሲያወሱ፦

​"ነገሩን ለማንሳት ያህል፣ በአንድ ወቅት አውሮፕላን ውስጥ ነበርኩ። አጠገቤ የነበረ ሰው የሶላት ወቅት ገና እንደገባ በአውሮፕላን ውስጥ መስገድ ጀመረ። እኛ ግን የምንጓዝበት ሀገር የሶላቱ ወቅት ሳይወጣ እንደርሳለን።
​ለእሱ ግዴታ የነበረበት ሶላቱን እስከ ወቅቱ መጨረሻ ማቆየት ነበር፤ በዚያም ሀገር ሲደርስ ሙሉ ሶላቱን ቂብላን ተቀጣጭቶና ቆሞ መስገድ ይችል ነበር። አሁን ግን (አውሮፕላን ውስጥ በመስገዱ) ቂብላን የመቀጣጨት መስፈርትን እና የመቆም (ቂያም) ግዴታን አጓድሏል።

​ጠየቅኩት፦ 'ለምን አሁን ትሰግዳለህ? ገና በወቅቱ መጀመሪያ ላይ ነን፣ ጅዳ አየር ማረፊያ ኢንሻአላህ ወቅቱ ሳይወጣ ደርሰን እንሰግዳለን' አልኩት።

​እሱም፦ 'አይ፣ እኔ ፈትዋ ጠይቄ እንዲህ ብለው ነው የመለሱልኝ' አለኝ።

​'ፈትዋ የሰጠህ ሰው ማነው?' አልኩት።
​እሱም፦ስልኩን አወጣ ከዛ 'ሼህ ጎግል (Google)!' ብሎ መለሰልኝ። እንደምታውቁት ማለት ነው።"

🌱 ​@TewhedandSuna

Comments

Be the first to add a comment