በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,274 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,759 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 79 ወንድ እና 50 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 10 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደት እና 1 ሰው ከአፋር ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 18 (11 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

ከዚህ ባለፈ ሁለት (2) በህክምና ማዕከል ውስት ህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ሶስት (63) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ60 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ30 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

@TenaET

1 comment

💔የበረሀዋ ነኝ💕
ከዱባይ ኮምቦልቻ ማረፍ ይቻላል ወይ ፕሊስ አድስ አበባ በሽታው ተስፋ ፍቷል