ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።
ኢንጅነር ሽመልስ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መርተዋል።
በተለያዩ የከፍተኛ ኃላፊነት ቦታዎችም ያገለገሉት ኢንጅነር ሽመልስ፣ በአዲሱ ኃላፊነታቸው የመንገድ ልማትን እንዲመሩ ተሹመዋል።
@etconp