መንገድ ላይ መፀዳዳት ለእስር ሊዳርግ ይችላል‼️በመንገድ ላይ የሚፀዳዳ ሰውን እስከ እስር የሚያደርስ ቅጣት መቅጣት የሚያስችል አዋጅ ለምክር ቤት እንደሚቀርብ ተገለጸ
‼️ከ20 ሚሊየን በላይ ወይም ከ17 በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን መንገድ ላይ እንደሚፀዳዱና የሃገሪቱን ገፅታ እያበላሸ መሆኑን ተከትሎ በአዋጅ መክልከል እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ባለፉት ዘመናትም ድርጊቱን የሚከለክሉ መመሪያዎች ቢኖሩም አሁን ላለው ሁኔታ አስቻይ እንዳልሆኑና የሃገሪቱን ገፅታ የሚያበላሹ ተግባራት በመሆናቸው እስከ እስር የሚያደርስ ቅጣት መቅጣት የሚያስችል አዋጅ ለምክር ቤት ለማቅረብ እያተዘጋጀ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የአካባቢ ጤና ፕሮግራም ዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ ተናግረዋል፡፡
አዋጁን ለምክር ቤት ለማቅረብ በቅድሚያ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአንዳንድ ምግብ ቤቶች የሚስተዋለው የመፀዳጃ ቤት እና የማብሰያ ክፍል አጠገብ ለአጠገብ መሆን ሌላኛው ችግር እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ በንግድ ፍቃድ አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ይስተዋላል ብለዋል፡፡ አዲሱ አዋጅ ይህንንም እንደሚያካትት ተናግረዋል፡፡
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
👇https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s