👉በግንባታ ላይ የእርጥበት እና የውሃ ሰርጎ መግባት (Water Seepage) የሚያመጣው ጉዳት💧

🌟​በምስሉ ላይ እንደምናየው በሰላብ ወይም በጣሪያ በኩል ሰርጎ በሚገባ እርጥበት ምክንያት የኮርኒሱ ቀለም ተላጥጦ እና የፕላስተር አካሉ ተፈረካክሶ ይገኛል። ይህ ችግር በቀለም ጥራት ማነስ ሳይሆን በውሃ መከላከያ (Waterproofing) እጥረት የሚፈጠር ነው።

🏛​የዚህ ዓይነቱ ችግር ዋና ዋና መንስኤዎች እና መፍትሄዎች፦

☄​ዋና ዋና መንስኤዎች፦

. ​ከላይኛው ወለል (Slab/Roof Top/Wet Area) የውሃ መከላከያ (Waterproofing Membrane) አለመኖር ወይም መሰነጣጠቅ።

. ​በሰላቡ ውስጥ የሚያልፉ የውሃ መስመሮች (Plumbing Pipes) መሾለክ ወይም መፍሰስ።

. ​ኮንክሪት ሲፈስ በቂ Compaction ባለመደረጉ የተፈጠሩ ጥቃቅን ቀዳዳዎች (Pores/Honeycombs)።

​መፍትሄዎች፦

.​Source Identification: በመጀመሪያ የውሃውን ምንጭ ማቆም (የውሃ መስመር ወይም የጣሪያ ውሃ መከላከያ ማስተካከል)።

. ​Scraping & Drying: የተላጣውን ቀለምና የላላውን ፕላስተር ሙሉ በሙሉ ስክራፕ አድርጎ ማስወገድና ቦታው በደንብ እንዲደርቅ ማድረግ።

. ​Waterproofing & Repainting: እርጥበት መከላከያ (Waterproofing Chemical/Primer) ከተቀባ በኋላ በድጋሚ ጂፕሰም/ፑቲ በማድረግ ጥራት ያለው ቀለም መቀባት።

🔆​በእርስዎ ቤት ወይም ሳይት ላይ ተመሳሳይ የውሃ ሰርጎ መግባት ያጋጥማችሁ ያውቃል? ችግሩን ለማስወገድ ምን ዓይነት Waterproofing Chemical ተጠቀማችሁ? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!

@etconp

Comments

Be the first to add a comment