👉​ የፍሊንትስቶንስ አ.ማ የረጅም ጊዜ የቤት ግዢ ክርክር በሰበር ሰሚ ችሎት ተቋጨ

​የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ለዓመታት ሲያከራክር የቆየውን የፍሊንትስቶንስ አ.ማ እና የደንበኞቹን የቤት ግዢ ውል ክርክር አስመልክቶ ውሳኔ ሰጥቷል።

🚧​የጉዳዩ መነሻ፡

በ2008 እና 2009 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ (ቦሌ በሻሌ ሳይት) ቤቶችን የገዙ 212 ደንበኞች፣ ድርጅቱ ቤቶቹን በወቅቱ ባለማስረከቡ ምክንያት ክስ መመስረታቸው ይታወሳል።

🔖​የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የሰበር ሰሚ ችሎት፣ ከዚህ ቀደም በግልግል ዳኝነት የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የሚከተለውን ብይን ሰጥቷል።

🏷​የካሳ ክፍያ፡

ፍሊንትስቶንስ አ.ማ በውሉ መሠረት ቤቶችን ባለማስረከቡ ለ103 ከሳሾች በድምሩ 224 ሚሊየን 430 ሺህ ብር የካሳ ክፍያ እንዲፈጽም ተወስኗል።

❇️​የስሌት መሠረት፡

ከሳሾች የጠየቁትን የገበያ ዋጋ (99,000 ብር በካሬ ሜትር) ውድቅ በማድረግ፣ ካሳው ሊሰላ የሚገባው ድርጅቱ ቤቶቹን ለማጠናቀቅ በጠየቀው የ24,500 ብር የካሬ ሜትር ዋጋ ልዩነት ላይ ተመስርቶ መሆኑን ችሎቱ አረጋግጧል።

🔗​ተመላሽ ገንዘብ፡

ከሳሾች ቀደም ብለው የከፈሉት ዋና ገንዘብ ከወለድ ጋር እንዲመለስላቸውም ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

▶️​ማስታወሻ፡ ቀሪዎቹ ከሳሾች ቀደም ባለው የግልግል ውሳኔ ተስማምተው አፈጻጸም ላይ እንደነበሩ ተገልጿል።

​ይህ ውሳኔ በሪል ስቴት ዘርፉ በውል ስምምነት እና በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ ትልቅ የህግ አርአያ የሚሆን ሆኗል።

🫵​ለተጨማሪ የኮንስትራክሽን ዘርፍ መረጃዎች እና ወቅታዊ የሪል ስቴት ዜናዎች 👇
​https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

Comments

Be the first to add a comment