👉ጥብቅ ማስጠንቀቂያ⚡️

🏷የመሬት መንሸራተት ስጋት በሚኪ ሌላንድ ኮንዶሚኒየም🚨

💫በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የሚኪ ሌላንድ (ብርጭቆ) ኮንዶሚኒየም አካባቢ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት እና የመሬት ስንጥቅ ምክንያት ከፍተኛ የጂኦቴክኒካል እና የመዋቅር (Structural) ስጋት እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

🚧በአካባቢው የታየው የመሬት መቀመጥ (Settlement)፣ የአስፋልት መሰንጠቅ እና እስከ 3 ሜትር የሚደርስ የመሬት መውረድ በአካባቢው ያሉ ህንፃዎች፣ መንገዶች እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ተጨማሪ ምርመራ እና አፋጣኝ የመከላከል ስራዎች እንዲካሄዱ ያስፈልጋል።

🧷እንደ ምህንድስና እይታ፣ በአካባቢው የጂኦቴክኒካል ጥናት፣ የSlope Stability Analysis፣ የውሃ ፍሰት ቁጥጥር (Drainage Improvement) እና አስፈላጊ የRetaining Structure ወይም የGround Stabilization ስራዎች በአፋጣኝ መተግበር ይገባል።

😱የሰው ህይወት እና ንብረት ደህንነት ከሁሉም በላይ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው አካላት በተቀናጀ መንገድ የምርመራ እና የማጠናከሪያ ስራዎችን እንዲያፋጥኑ ይጠበቃል።

#CivilEngineering #GeotechnicalEngineering #SlopeStability #StructuralSafety #AddisAbaba #CondominiumSafety

@etconp

Comments

Be the first to add a comment